ለተለያዩ የእድሜ እርከን የተለያዩ የቁጠባ አማራጮች ከባንካችን

ለተለያዩ የእድሜ እርከን የተለያዩ የቁጠባ አማራጮች ከባንካችን

እንደሚከመር የድንጋይ ካብ የብዙ ትናንሽ ጡቦች አገርን ይገነባሉ፤ አገር ትንሽ በሚመስሉ ግን ትልቅ ዋጋ ባላቸው ሰዎች (ጡቦች) ትገነባለች። የሰዎች ስብስብ ደግሞ ሕዝብን ይፈጥራል፤ ሕዝብ በባሕርይው ኃይል ነው። እኛ ነገ፣ ምንም ማድረግ የሚያስችለንን አቅም የሚፈጥርልን፣ ዛሬ በምናደርገው ጥቂት ተግባር ነው። ተግባር ደግሞ ከአሁን ይጀምራል።

አሁን ስለሚጀመር ጥቂት ተግባር ላውጋችሁ፣

ቁጣባ፣ ዛሬ በምናስቀምጠው ጥቂት ገንዘብ ነገን የምንፈጥርበት ትልቅ ኃይል (ሀብት) ነው። አብዛኞቻችን አሁን እንዲኾን የምንሻቸው ነገሮች አሉን፤ ግን አንችልም። ብዙ ጊዜ ማድረግ የምንችላቸውን ጉዳዮች በገንዘብ ምክንያት ነገዎቻችን ተበላሽተውብናል። እስኪ በገንዘብ ምክንያት ያጣናቸውን ጉዳዮች እናስብ…… የትምህርት ቤት ክፍያ፣ አነስተኛ ንግድ ለመጀመር፣ ቤት ለመግዛት፣ መንጃ ፍቃድ ለማውጣት፣ የወደድናቸውን ነገሮች ለመግዛት፣ ያሉብንን ብድር ለመክፈል፣ … ወዘተ ማድረግ ያልቻልናቸው ማቃቶች ናቸው። ታዲያ ከችግሮቻችን እንዴት መቅደም እንችላለን? ለዚህ ኹሉ ጥያቄ ቁጠባ መልስ ይሰጣል።

ቁጠባ መሠረታዊ ገንዘብ የመቆጣጠር ችሎታን ያዳብራል፡፡ ይህን ችሎታ የምናዳብረበት መንገድ ደግሞ ግብ፣ የጊዜ ሰሌዳና የገንዘብ መጠን በመወሰንና በማቀድ ነው፡፡ ግብ፣ የጊዜ ሰሌዳ እና የገንዘብ ተመን ያሰቡትን እንዲያሳኩና የቁጠባ ባህልን እንዲፈጥሩ ያግዛሉ።

እንዴት?….በቅድሚያ ግልጽ የሆነ ግብ ያስቀምጡ፤ ግብዎን ለማሳካት የጊዜ ሰሌዳና የሚያስፈልገውን የገንዘብ መጠን ይወስኑ። ምናልባት ትንሽ ገንዘብ በመቆጠብ፣ በባንክ ውስጥ የቁጠባ ሒሳብ ይክፈቱ። በገቢዎን መጠን ለመቆጠብና ምን ያህል ጊዜ እንደሚወስድብዎት ማወቅ ይችላሉ።

የሚፈልጉትንና የሚያስፈልግዎትን ጉዳዮች መለየት የቁጠባ መንገዶቻችንን ያቀሉልናል። መሠረታዊ ፍላጎቶቻች መሟላት የሚገባቸው ናቸው፡፡ ከመሠረታዊ ፍላጎቶች በላይ የኾነ ማንኛውም ነገር “ተጨማሪ” ነው። ሁል ጊዜ ከሚያስፈልገን በላይ መሆን መልመድ አለብን። ይኽንን ለመልመድ ራስን አለማወዳደር ነው፡፡ ምክንያቱም ንፅፅር የደስታ ሌባ ነው፡፡ ከሌሎቹ ጋር በየጊዜው ያለንን እያነጻጸርን ከሆነ በጭራሽ አንረካም።

ወደ ግቦት ባስቀመጡት የጊዜ ሰሌዳ እንዲጓዙ ከፈለጉ ገንዘብን እንዴት እንደሚያገኙ ይወቁ፡፡ ከመደበኛ የሥራ ሰዓት በተጨማሪ የትርፍ ሰዓት ሥራ በመሥራት ገቢዎን ያሳድጉ።

አገርኛ ብሒላችን ‹‹ገንዘብ በሃያ ዓመት›› እንደሚለው፣ ወጣቶች በትኩስ ጉልበታቸው ገንዘብ የማካበት ዓቅማቸውን እንዲያዳብሩ፤ ልብ ብቻ ሳይኾን ሀብትንም በዐርባ ዓመት እንዲታደሉ ከወዲኹ ፍኖቱን (መንገዱን) እንዲያበጁ ለአረጋውያን፤ በተለያዩ መልኩ የቀረቡ የቁጠባ አማራጮች ከአጓጊ ጥቅሞች ጋር ባንካችን አቅርቦልናል።

አቢሲንያ ባንክ ነገን የመገንባት ዓቅም ለማዳበር የሚያስችል የቁጠባ መንገድ በተለያዩ አማራጭ እንካችኹ ብሎናል። ባንካችን በተለያዩ የእድሜ ዕርከን ላይ ለሚገኙ በልዩ ኹኔታና ከፍ ባለ ወለድ የተለያዩ የቁጠባ አማራጮችን አቀረበልን።

ልጆችዎ በልጅነታቸው የቁጠባ ልምድን እንዲያዳብሩና ከወዲሁ የቁጠባን አስፈላጊነት የሚስተምር የቁጠባ ሒሳብ፡፡

  • ለታዳጊዎች (Accounts for Minors) የቁጠባ አማራጭ

ከ14-17 ዓመት ላሉ ታዳጊዎች የቀረበ በየወሩ ከ25 ብር ጀምሮ መቆጠብ የሚያስችል ልዩ የቁጠባ ደብተር

ለሴቶች የተዘጋጀ ልዩ ስጦታ፤ ከፍ ባለው የወለድ ተመን የቀረበ የቁጠባ ሒሳብ፡፡ በዚህ የቁጠባ ሒሳብ ሴቶች በሕይወታችን ውስጥ ለሚኖራቸው ሚና ለማገዝ፤ የግል ንግድ ለመክፈት ለሚስቡ በልዩ ኹኔታ ቀረበ የቁጠባ ደብተር፡፡

ለስኬታማነትና ከድህነት መውጫ ቁልፍ መሣሪያ የኾነውን ትምህርት፤ የትምህርት ቁጠባ ሒሳቡ፡፡

ለጡረተኞች የተዘጋጀ የቁጠባ ደብተር፤

ነገን ከአኹን እንጀምር።

አቢሲንያ ጋር ነገ እንደርሳል!

ምኒልክ ብርሃኑ

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Call Now Button