ተሸለሙ!

ተሸለሙ!

ባንካችን ከአለም አቀፉ የሴቶች ቀን “ማርች 8” ጋር በተያያዘ ‘’እችላለሁ’’ በሚል መሪ ቃል ባከናወነው የግጥም እና የሙዚቃ ውድድር ላይ በየዘርፉ ከ1ኛ-3ኛ ለወጡት ተወዳዳሪዎች ሚያዚያ 12 ቀን 2014 ዓም. በግሮቭ ጋርደን ባዘጋጀው መርሃ ግብር ላይ ሽልማትና የምስክር ወረቀት አበርክቷል፡፡
በዚህ መርሃ ግብር የድምፅና የግጥም ተሰጥኦ ያላቸው እንስቶች እንዲወዳደሩ በማድረግ ስራቸውን ካቀረቡት 33 የድምፅ ተወዳዳሪዎችና 318 የግጥም ተወዳዳሪዎች መካከል በዳኞችና በአድማጭ ተሳታፊዎች ከፍተኛ ድምፅ ያገኙት ሶስት ሶስት አሸናፊዎች ተለይተው ለሽልማት በቅተዋል፡፡
በሥነስርዓቱም በሁለቱም ዘርፍ 1ኛ ለወጡት የብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር)፣ 2ኛ ለወጡት የብር 30,000.00(ሠላሳ ሺህ ብር) እንዲሁም 3ኛ ለወጡት የብር 20,000.00 (ሃያ ሺህ ብር) ሽልማት የተበረከተ ሲሆን በፕሮግራሙም ላይ አሸናፊዎች ያሸነፉበትን የግጥም እና የሙዚቃ ስራዎቻቸውን አቅርበዋል፡፡
በሌላ በኩል የውድድሩ ሌላኛው አካል በነበረው የተሻለ የሥራ ፈጠራዎችን የማቅረብ ውድድር ላይ ለአሸናፊዎቹ ከገበያው በአነሰ የወለድ ምጣኔና ካለመያዣ እስከ ብር 300,000.00 (ሦስት መቶ ሺህ) ድረስ ብድር መመቻቸቱ ተገልጿል፡፡ ለሙሉ ይዘቱ ከዚህ ጋር ተያይዞ የሚገኘውን መስፈንጠሪያ በመጠቀም ቪዲዮውን ይመልከቱ https://youtu.be/Zd542_4WVPg

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Call Now Button