የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

አቢሲንያ ባንክ /አ.ማ/ ለሰጠው ብድር በዋስትና የያዘውንና በሠንጠረዡ የተመለከቱትን ንብረቶች በአዋጅ ቁጥር 97/90 (እንደተሻሻለው) መሠረት ንብረቶቹ ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ተጫራቾች ለጨረታ ከመቅረባቸው በፊት የሚከተሉትን ደንቦች መገንዘብ ይኖርባቸዋል፡፡

  • ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ንብረት የጨረታ መነሻ ዋጋውን ¼ (አንድ አራተኛ) በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይም ሲ.ፒ.ኦ በአቢሲንያ ባንክ (አ.ማ) ስም በማሰራት ለጨረታ ማስከበሪያ በማስያዝ በጨረታው ለመሳተፍ ይችላሉ፡፡
  • የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱ ከባንኩ በደብዳቤ ከተገለጸለት ቀን ጀምሮ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ በ15 (አስራ አምስት) ቀናት ውስጥ አጠቃሎ ከፍሎ በጨረታ ያሸነፈበትን ንብረት/ንብረቶች መረከብ ይኖርበታል፡፡ በእነዚህ ቀናት ውስጥ ካልከፈለ ጨረታው ተሰርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል፡፡ በጨረታው ለተሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ ይመለስላቸዋል፡፡
  • ተበዳሪው/መያዣ ሰጪው በሐራጁ ቀንና ሰዓት በቦታው መገኘት ይችላሉ፡፡ ነገር ግን ባይገኙ ሐራጁ በሌሉበት ይካሄዳል፡፡
  • የጨረታው አሸናፊ ከሚገዛው ንብረት ጋር የተያያዙ ማናቸውም ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎችን ፣ ግብር ዋጋ ላይ የሚታሰብ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ 15% እንዲሁም ከስም ዝውውር ጋር የሚገናኙ ማናቸውም ወጪዎች ገዢ ይከፍላል፡፡ ቋሚ ንብረትን በተመለከተ ውዝፍ የሊዝ ክፍያ ባንኩ የሚከፍል ሲሆን ቀሪ የሊዝ ክፍያ ዕዳ ደግሞ ወደ አሸናፊው/ገዢ የሚተላለፍ ይሆናል፡፡
  • ንብረቶቹን በሥራ ሰዓት ፕሮግራም አሲዞ ለመጎብኘት ወይም ለማየት ይቻላል፡፡
  • በባንኩ ብድር ፖሊሲ እና መመሪያ መሠረት መስፈርቱን ለሚያሟሉ የጨረታው ከፍተኛ ዋጋ አቅራቢዎች ባንኩ ከፊል ብድር ሊሰጥ ይችላል፡፡
  • የጨረታው ቦታ አ.አ ከተማ ቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ 4 ህብረት ባንክ አ.ማ ዋና መስሪያ ቤት ጎን ካለው አልፓውሎ ህንጻ 3ኛ ፎቅ በባንኩ ህግ መምሪያ ነው፡፡
  • ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0115-150711 እና 0115 54 67 37/36 አ.አ በመደወል መጠየቅ ይቻላል፡፡
  • ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ 
 የተበዳሪው ስምከተበዳሪው የሚፈለግበት ቀሪ ዕዳ የመያዣ ስጪው ስምየንብረቱ ዓይነትና አገልግሎትየቦታው ስፋትየባለቤትነት ማረጋገጫ ካርታ ቁጥር ንብረቱ የሚገኝበት አድራሻ የጨረታ መነሻ ዋጋ በብር ጨረታው የሚካሄድበት ቀን  የምዝገባ ሰዓትየጨረታ ሰዓትጨረታው የወጣበት ጊዜ
  1ወ/ት ከድጃ አህመድእስከ ግንቦት 24 ቀን 2011ዓ.ም ድረስ    ብር 19,922,783.24 አቶ አወል ሀሰንመኖሪያ ቤት B+G+3183 ካ.ሜቦሌ10/60/104-4767/292865/01አ.አ ቦሌ ክ/ከተማ12,323,350.00ግንቦት 12 ቀን 2013 ዓ.ም4:30-5፡305፡30-6፡00  በድጋሚ
  2ጂ.ዜድ.ኤ ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበርእስከ ህዳር 18 ቀን 2012 ዓ.ም ድረስ ብር126,537,046.20ቢንያም ቢቢ እና ኤፍሬም ቢቢጅምር መኖሪያ ቤት427 ካ.ሜ06097/4አ.አ አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ      ወረዳ 01 8,099,610.68ሚያዚያ 29 ቀን 2013 ዓ.ም4:30-5፡305፡30-6፡00  ለመጀመሪያ

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Call Now Button