የ “እችላለሁ” ዘመቻ የሙዚቃ ሥራዎች ምርጫ ላይ ይሳተፉ!

የ “እችላለሁ” ዘመቻ የሙዚቃ ሥራዎች ምርጫ ላይ ይሳተፉ!

በግጥም ስራዎች ላይ የሚደረገው ምርጫ ተጠናቋል፣ አሁን ደግሞ በሙዚቃ ምርጫ ላይ ይሳተፉ!

ማርች 8 የሚከበረውን የሴቶች ቀን አስመልክቶ ሴት ባለተሰጥኦዎችን በማሳተፍ በባንካችን ሲካሄድ የነበረው የ “እችላለሁ” ዘመቻ የውድድር ሥራዎች ማቅረቢያ ቀን እሑድ መጋቢት 11 ቀን 2014 ዓ.ም. የተጠናቀቀ ሲሆን፣ በውድድሩም 318 በግጥም፣ እንዲሁም 33 በድምፅ በአጠቃላይ 351 ተሳታፊዎች ስራቸውን አቅርበዋል፡፡ ለውድድር ከቀረቡት የሙዚቃና የግጥም ስራዎች ውስጥም ከእያንዳንዱ ዘርፍ አስር አስር ስራዎች በባለሙያዎች ተገምግመው ለመጨረሻው የታዳሚዎች ምርጫ የተለዩ ሲሆን፣ አርቲስት ጌትነት እንየው፣ ገጣሚ ረድኤት ተረፈ እና ገጣሚ የሺወርቅ ወልዴ የግጥም ስራዎችን በመገምገም፣ እንዲሁም ሙዚቀኛ የሹምነሽ ታዬ እና ሙዚቀኛ ሜሮን ረጋሳ የሙዚቃ ስራዎችን በመገምገም ስራ ላይ ተሳትፈዋል፡፡በቀጣይም ከእያንዳንዱ ማለትም ከግጥምና ሙዚቃ ዘርፍ ከአንደኛ እስከ ሶስተኛ የሚወጡት ባለተስጥኦዎች በአድማጭና አንባቢ ድምፅ 50% ፣እንዲሁም በዳኞች 50% ነጥብ የሚለዩ ይሆናል፡፡
በመሆኑም በመጀመሪያ ዙር የተለዩት አስር የሙዚቃ ስራዎች በፌስ ቡክ ገፃችን ላይ የቀረቡ በመሆኑ ይህን ሊንክ በመጠቀም https://fb.watch/c7Rm3F8uXy/ ከዛሬ መጋቢት 24፣ 2014 እስከ መጋቢት 27 ቀን 2014 ባለው ጊዜ ውስጥ የተወዳዳሪዎችን በምስሉ ላይ የሚገኘውን መለያ ኮድ በመጠቀምና የመረጣችሁትን በኮመንት ሥፍራ ላይ በመፃፍ የድምፅ አሰጣጥ ተሳትፎ እንድታደርጉ እንጋብዛለን፡፡
መልካም ዕድል ለተሳታፊዎች!
በግጥም ስራዎች ላይ ምርጫ በማካሄድ የድምጽ ተሳትፎ ላደረጋችሁ እናመሰግናለን፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Call Now Button