የ1ኛ ዙር (2014 ዓ.ም) እችላለሁ ዘመቻ የሴቶች ሥራ ፈጣሪ የተሸላሚዎች ጉዞ!

የ1ኛ ዙር (2014 ዓ.ም) እችላለሁ ዘመቻ የሴቶች ሥራ ፈጣሪ የተሸላሚዎች ጉዞ!

ባንካችን አቢሲንያ የአለም አቀፉን የሴቶች ቀን(ማርች 8) በማስመልከት ለ2ኛ ጊዜ ‘’እችላለሁ’’ በሚል መሪ ቃል ልዩ ልዩ ውድድሮችን ከየካቲት 29 እስከ መጋቢት 13 እያከናወነ ይገኛል፡፡በዚህ ውድድርም በግጥም፤በሙዚቃ፤ በቲክቶከሮች መካከል የሚደረግ ውድድር የሚከናወን ሲሆን ከዚህ በተጨማሪ ለሀምሳ የስራ ፈጣሪ ሴቶች ዝቅተኛ ወለድ የሚታሰብበት ያለመያዣ ለእያንዳንዳቸው የብር 500,000(አምስት መቶ ሺ ብር) ብድር አዘጋጅቷል፡፡ ባለፈው ዓመት በተመሳሳይ በተደረገው ውድድር ለ27 ሴት ስራ ፈጣሪዎች ለእያንዳናዳቸው የብር 300,000(ሶስት መቶ ሺ ብር) ብድር ማመቻቸቱ የሚታወስ ሲሆን ለዛሬ ከእድሉ ተጠቃሚዎች ጋር የተደረገውን አጭር ቆይታ ይዘንላችሁ ቀርበናል፡፡

ወ/ሮ ሃና ቤጊ የባንካችን መካከለኛው ዲስትሪክት ጎፋ ማዞሪያ ቅርንጫፍ ደንበኛ ሲሆኑ ባለፈው አመት ማርች 8 ቀን 2022 አስመልክቶ ባንኩ ለስራ ፈጣሪ ሴቶች ያዘጋጀውን  የብር 300,000.00 ብድር ተጠቃሚ ናቸው ፡ ከደንበኛዋ ጋር ያደረግነውን አጭር ቃለ መጠይቅ እንድትከታተሉ ተጋብዛችኋል፡፡

ጠያቂ-በመጀመሪያ እንኳን በየዓመቱ ለሚከበረው ማርች 8 የሴቶች ቀን አደረሶት

ደንበኛ- አመሰግናለሁ

ጠያቂ-በመጀመሪያ ስምዎትን እና በምን ስራ ላይ ተሰማርተው እንደሚገኙ ቢገልጹልን?

ደንበኛ ወ/ሮ ሃና ቤጊ እባላለሁ፡ የተሰማራሁበት የስራ ዘርፍ ደግሞ ዳቦ እና እንጀራ ማቀነባበር ነው በስራውም ወደ ዘጠኝ አመት ያክል ቆይቼበታለሁ፡፡

ጠያቂ- ባለፈው አመት ተዛጋጅቶ የነበረውን ውድድር እንዴት ሰሙ ፡ እርሶስ በምን አይነት መልኩ ተሳተፉ?

ወ/ሮ ሃና – የሚገርመው ነግር እኔ ስለውድድሩ በሬድዮ ነበር የሰማሁት የውድድሩ ፕሮፖዛል መቀበያ ቀን ቅዳሜ ሊያልቅ ሀሙስ ቀን ነው በሬድዮ ያዳመጥኩት፡ በዛን ወቅት መወዳደሪያ ሰነዱ ዲስትሪክት ላይ ስለነበር የሚገባው ፕሮፖዛሌን በእጄ ጽፌ  በኮምፒውተር ተገልብጦ እስከሚያልቅ ቅዳሜ የማስገቢያው ሰዓት ደርሶብኝ ባለቀ ሰዓት ነበር ያስገባሁት፡ በዚህ አጋጣሚ ድስትሪክቱ ስለተባበረኝ አመሰግናለሁ፡፡

ጠያቂ– ባንኩ በየዓመቱ የሚከበረውን ማርች 8 የሴቶች ቀንን አስመልክቶ ያለ ብድር መያዣ/ዋስትና/ እና አነስተኛ ወለድ ብድር ሲያበድሮት ምን ተሰማዎት?

ወ/ሮ ሃና- ማርች 8 አስመልቶ አቢሲንያ ባንክ ሴቶችን ለመደገፍ ያደረገው ነገር ድርጅታችንን በጣም ጠቅሞታል፡ አቢሲንያ ከባንክም በላይ ሰው ላይ የሚሰራ ድርጅት መሆኑን ተረድተናል በራሳችን ተሰጥኦ/ስራ ፈጠራ/ ብቻ ላይ ተመስርቶ ባደረገው እገዛ በጣም ነው ደስ ያለኝ፡፡

ጠያቂ – ብድሩን ከወሰዱ በኋላ በስራዎ እና በኑሮዎ ላይ ምን ለውጥ አመጡ ?

ወ/ሮ ሃናበወቅቱ ያለምንም መያዣ የተሰጠን ገንዘብ 300,000.00 /ሶሰት መቶ ሺህ ብር/ ነበር ፡ በወቅቱ ጥሬ እቃ እንድንገዛበት በደንብ አግዞናል ፡ ድርጅቱን በፋይናንስ ለመደገፍ ረድቶናል፡ የድርጅቱ ምርታማነት ጨምሯል እንዲም በቂ የሆነ ለድርጅቱ የሚያስፈልጉ ግብአቶችን /stocks/ እንድንይዝ ከመጥቀሙም ባሻገር ተጨማሪ ሰራተኞችን እንድንቀጥር እና በፊት ዳቦ ቤት ብቻ የነበረውን ድርጅት ዱቄት፡የጤፍ እና ጥራጥሬ ውጤቶችንም ለመጨመር  ምንያት ሆኖናል ፡፡

ጠያቂ- ብድሩን ካገኙ በኋላ ለቁጠባ ያሎት አመለካከት / አስተያየት ምን ይመስላል

ወ/ሮ ሃና- በመጀመሪያ ለባንክ ያለኝ አመለካከት ተቀይሯል ፡ ከአቢሲንያ ባንክ ጋር መስራት ማለት ከመቆጠብም ባሻገር ለሽልማት እንደሚያበቃ ተረድቻለሁ ደግሞም ሴቶችን የሚደግፍ ባንክ መሆኑን እንዳውቅ ረድቶኛል በዚህ ራሴ አሁንም ድረስ በባንኩ ከመቆጠቤም ባሻገር፤ በድርጅታችን ባህላዊ ዳቦ/ ድፎ ዳቦ / ሊያስጋግሩ ለሚመጡ ሰዎች ስለቁጣባ ጠቃሚነት እያሰረዳሁ ክፍያቸውንም በአቢሲንያ ሞባይል ባንኪንግ እንዲያስተላልፉ እየተናገርኩ እገኛለሁ፡፡

ጠያቂ ፡ ለዘንድሮ የስራ ፈጠራ ተወዳዳሪዎች የሚያስተላልፉት መልዕክት ካለ

ወ/ሮ ሃና- የዘንድሮው ብድር ወደ ብር 500,000.00 እንዳደገ ሰምቻለሁ ይሄ በጣም ጥሩ እድል ነው ባንኩም ታማኝ እና ቃሉን የሚያከብር በመሆን እንደዚሁም ብድር  የመመለሻው ጊዜም በቂ በመሆኑ ሌሎች ሴቶች እንደ እኔ እድሉን እንዲጠቀሙበት እያሳሰብኩ፡ ባንኩም በደንብ የማስታወቂያ ተደራሽነቱን እንዲያሰፋና ማመልከቻ/ ፕሮፖዛል/ የመቀበያ ጊዜውንም ጨመር  ቢያደርገው የሚል መልዕክት ነው ያለኝ፡፡

ጠያቂ- አመሰግናለሁ

ወ/ሮ ሃና- እኔም አመሰግናለሁ 

//

ወ/ሮ ትዕግስት አየልኝ የባንካችን ባህርዳር ዲስትሪክት ጣና ቅርንጫፍ ደንበኛ ሲሆኑ ባለፈው አመት ማርች 8 ቀን 2022 አስመልክቶ ባንኩ ለሴት የስራ ፈጣሪዎች ያዘጋጀውን  የብር 300,000.00 ብድር ተጠቃሚ ናቸው ፡ ከደንበኛዋ ጋር ያደረግነውን አጭር ቃለ መጠይቅ እንድትከታተሉ ተጋብዛችኋል፡፡

ጠያቂ-በመጀመሪያ እንኳን በየዓመቱ ለሚከበረው ማርች 8 የሴቶች ቀን አደረሶት

ደንበኛ- አመሰግናለሁ

ጠያቂ-በመጀመሪያ ስምዎትን እና በምን ስራ ላይ ተሰማርተው እንደሚገኙ ቢገልጹልን?

ደንበኛ- ስሜ ወ/ሮ ትዕግስት አየልኝ ይባላል ፡ የተሰማራሁበት ስራ ዘርፍ የተፈጥሮ አበባ ሽያጭ ፡ የዲኮር እና የሰርግ ልብሶች ኪራይ አግልግሎት ነው፡፡

ጠያቂ– ባንኩ በየዓመቱ የሚከበረውን ማርች 8 የሴቶች ቀንን አስመልክቶ ያለ ብድር መያዣ/ዋስትና/ እና አነስተኛ ወለድ ብድር ሲያበድሮት ምን ተሰማዎት?

ወ/ሮ ትዕግስት- እጅግ በጣም ትልቅ ደስታ ነው የተሰማኝ ፡ አቢሲንያ ባንክ ይህን እድል ስላመቻቸልኝ ባንኩን አመሰግናለሁ፡፡

ጠያቂ – ብድሩን ከወሰዱ በኋላ በስራዎ እና በኑሮዎ ላይ ምን ለውጥ አመጡ ?

ወ/ሮ ትዕግስት- ባንኩ በሰጠኝ እድል በእቅድ ደረጃ ላይ የነበሩ ስራዎቼን ማስፋፋት ችያለሁ፡ በዚህም ባንኩ ትልቅ ባለውለታዬ ነው፡፡

ጠያቂ- ብድሩን ካገኙ በኋላ ለቁጠባ ያሎት አመለካከት / አስተያየት ምን ይመስላል ?

ወ/ሮ ትዕግስት- ቁጠባ በንግድ ውስጥም ሆነ ከንግድ ውጪ ላለ ሰው ሁሉ ጠቃሚ በመሆኑ  ፡ ሁሉም የአቢሲንያ ደንበኛ መቆጠብ እና መሸለም ወይንም ለመሸለም ሁሌም ዝግጁ መሆን አለበት የሚል አስተያየት ነው ያለኝ፡፡

ጠያቂ– ወደ ፊት ከአቢሲንያ ጋር ምን ሊሰሩ አስበዋል ?

ከአቢሲንያ ባንክ ጋር ካለኝ ደንበኝነት አንጻር የጀመርኩትን መኖሪያ ቤት በመጨረስ፡ የተጀመረውን የስራ ዘርፍ ወደ ትልቅ ደረጃ ማሸጋገር አስቤያለሁ፡፡በዚህ አጋጣሚ ባንኩ በቅርቡ በባህርዳር ከተማ ባዘጋጀው የግማሽ ዓመት የዕቅድ ክንውን ግምገማ ወቅት በነበረው የአዳራሽ ማስዋብ ስራ ላይ እንድሳተፍም እድሉን ስላመቻቸልኝ ለማመስገን እወዳለው፡፡

ጠያቂ – ለዘንድሮ የስራ ፈጠራ ተወዳዳሪዎች የሚያስተላልፉት መልዕክት ካለ ?

ወ/ሮ ትዕግስት- ዘንድሮ ለሚወዳደሩት መልካም እድል እየተመኘሁ ባንኩ ሌሎች ተጨማሪ ሽልማቶችንም በውድድሩ እንዲያካትት መልእክቴን እያስተላለፍኩ ፡ ስለተደረገልኝ ሁሉ በድጋሚ ባንኩን ማመስገን እፈልጋለሁ፡፡

ጠያቂ ፡- አመሰግናለሁ

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Call Now Button