ባንካችን አቢሲንያ 16ኛውን የቨርቹዋል ባንኪንግ ማዕከል በብስራተ ገብርኤል አካባቢ አስመረቀ!

ባንካችን አቢሲንያ 16ኛውን የቨርቹዋል ባንኪንግ ማዕከል በብስራተ ገብርኤል አካባቢ አስመረቀ!

ይህ አዲሱ ዘመናዊ የአገልግሎት ማዕከል (Virtual Banking Center) ፣ በብስራተ ገብርኤል እና አካባቢው ለሚገኙ የባንካችን ደንበኞች አገልግሎቱን ተደራሽ የሚያደርግ ሲሆን፣ በአዲስ አበባ የሚገኙትን የቨርቹዋል ማዕከላት ወደ 9 ከፍ አድርጎታል፡፡

ማዕከሉ አዲስ በሆነ #Interactive_Teller_Machine (ITM) ቴክኖሎጂ የሚታገዝ ሲሆን፤ አንድ የባንክ ቅርንጫፍ የሚሰጣቸውን በርካታ አገልግሎቶች ከባንካችን የደንበኞች ግንኙነት ማዕከል ጋር ግንኙ ሆኖ ተጠቃሚዎች በጊዜ ሳይገደቡ ከእሑድ እስከ እሑድ በቀን ለ24 ሰዓታት ልዩ አገልግሎት የሚያገኙበት ነው፡፡

ዘመናዊ የባንክ አገልግሎቶችን  ከአቢሲንያ ባንክዎ ያግኙ!

የማዕከሉ አድራሻ፡ ብስራተ ገብርኤል፣ የአፍሪካ ኢንሹራንስ ህንጻ ሥር

#አቢሲንያ_የሁሉም_ምርጫ!

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Call Now Button