አቢሲንያ ባንክ በአቢሲንያ አሚን በኩል ለ2ተኛ ጊዜ ያዘጋጀው አሚን አዋርድ የስራ ፈጠራ ውድድር የማስጀመሪያ መርሃ ግብር ተካሄደ፡፡

አቢሲንያ ባንክ በአቢሲንያ አሚን በኩል ለ2ተኛ ጊዜ ያዘጋጀው አሚን አዋርድ የስራ ፈጠራ ውድድር የማስጀመሪያ መርሃ ግብር ተካሄደ፡፡

ባሳለፍነው አመት የመጀመሪያውን ዙር በደማቅ ሁኔታ ተካሂዶ የነበረው አሚን አዋርድ የስራ ፈጠራ ውድድር በጠቅላላው መስፈርት ያሟሉ 86 ተወዳዳሪዎች ተሳትፈውበት በዳኞች መስፈርት ተመዝነው በየዙሩ የሚሰናበቱትን ተወዳዳሪዎች ጨምሮ ወደመጨረሻው ዙር የደረሱት አምስት ተወዳዳሪዎች እንደየደረጃቸው ከ ሁለት መቶ ሺ እስከ አንድ ሚሊዮን ብር ሸልሞ መጠናቀቁ የሚታወስ ነው ፡፡
ይህ በአቢሲንያ ባንክ በአቢሲንያ አሚን ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት በኩል የተሰናዳው አሚን አዋርድ የስራ ፈጠራ ውድድር ወጣት፣ ሴት እና በተጨማሪም አካል ጉዳተኛ ሥራ ፈጣሪዎችን በማነሳሳት ጉልህ ሚና እንደ ነበረው፣ ይህን ውድድር በማዘጋጀቱ ማኅበራዊ ኃላፊነቱን መወጣቱን እንዲሁም፣ በሕዝብም ዘንድ ተጨማሪ እውቅናን ያስገኘለትና አቢሲንያ አሚን ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎቱን በማስተዋወቅ ረገድም ከፍተኛ ድርሻ የነበረው መሆኑን በርካቶች ምስክርነት ሰጥተዋል ፡
በመጀመርያው ዙር ከመላው ሀገሪቱ ወደ አዲስ አበባ በመምጣት ውድድራቸውን ሲያደርጉ የነበሩ ተወዳዳሪዎችን ያሰተናግድ የነበረው ውድድር በሁለተኛው ዙር ከአዲስ አበባው በተጨማሪ በደሴ እና በድሬደዋ ከተሞችም ውድድሩ የሚከናወን ሲሆን ሌሎች በርካታ አዳዲስ ነገሮችን ጨምሮ አሚን አዋርድ አዲስ አበባ በሚገኘው በስቴይ ኢዚ ፕላስ ሆቴል በሁለተኛ ዙር ዳግም መመለሱን ባበሰረበት ወቅት የባንኩ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች፤ የባንኩ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት እንዲሁም የባንኩ የሸሪአ ቦርድ አማካሪዎች፤ ከስራ ፈጠራና ክህሎት ሚኒስቴር የስራ መሪዎች የሚዲያ አካላት በተገኙበት በደማቅ ሁኔታ ተከብሮ ውሏል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Call Now Button