በ “መቆጠብ ያሸልማል” ና “የእንሸልምዎ” የዕጣ አወጣጥ ስነስርአት ተካሄደ!

በ “መቆጠብ ያሸልማል” ና “የእንሸልምዎ” የዕጣ አወጣጥ ስነስርአት ተካሄደ!

ባንካችን አቢሲንያ የአገር ውስጥ ቁጠባን እና የውጭ ምንዛሬን ለማሳደግ ለ4ተኛ ጊዜ መቆጠብ ያሸልማል በሚል መርሃ ግብር እንዲሁም ለ5ተኛ ጊዜ ያዘጋጀው የእንሸልምዎ ፤ሽልማት የሚያስገኝ መርሐ-ግብርን አስመልክቶ በዛሬው ዕለት በብሔራዊ ሎተሪ አዳራሽ የዕጣ አወጣጥ ሥነ-ሥርዓት አከናወነ፡፡
በዕጣ አወጣጥ ስነ ስርአቱ ላይ የባንካችን የሥራ አመራር አባላት፣ የብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር ሠራተኞችና ታዛቢዎች፣ የሚዲያ አካላትና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት የብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር አዳራሽ በዛሬው ዕለት የዕጣ አወጣጥ ሥነ-ሥርዓቱ በይፋ ተከናውኗል፡፡
የአገር ውስጥ ቁጠባን ለማሳደግ ‹‹መቆጠብ ያሸልማል›› በሚለው መርሐ-ግብር በአንደኛ ዕጣ ከተቀመጠው አይሱዙ ኤንፒአር እድለኛ ጀምሮ በስምንተኛ ዕጣ እስከ ተቀመጡት ስማርት ስልኮች ድረስ 160 ባለ ዕድለኞች ተለይተው ታውቀዋል፡፡ በተመሳሳይ የውጭ ምንዛሬን ለማሳደግ ‹‹እንሸልሞ›› በሚለው መርሐ-ግብር በአንደኛ ዕጣ ከተቀመጠው በቱርክ የ5 ቀናት ቆይታ ሙሉ ወጪያዎች የሚሸፈንላቸውን እድለኛ ጀምሮ በዘጠነኛ ዕጣ እስከ ተቀመጡት ያልተገደበ የአንድ ዓመት የዋይፋይ አገልግሎት ክፍያ ድረስ 27 ባለ ዕድለኞች ተለይተው ታውቀዋል፡፡
ባለ ዕድለኛ ደምበኞቻችን እንኳን ደስ አላችሁ!!

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Call Now Button