አቢሲንያ ባንክ እና ሳፋሪ ኮም ኤም ፔሳ በትረስት አካውንት፣ በሞባይል ባንኪንና በወኪል አጋርነት ዙሪያ አብሮ ለመስራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራረሙ፡፡

አቢሲንያ ባንክ እና ሳፋሪ ኮም ኤም ፔሳ በትረስት አካውንት፣ በሞባይል ባንኪንና በወኪል አጋርነት ዙሪያ አብሮ ለመስራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራረሙ፡፡

አቢሲንያ ባንክ ከሳፋሪ ኮም ኤም ፔሳ ጋር በኢትዮጵያ ዘርፈ ብዙ የዲጂታል ፋይናንስ አቅርቦቶችን ማቅረብ የሚያስችል የትብብር ስምምነት ተፈራረመ፡፡በተደረገው ስምምነት መሠረት በሁለቱ አካላት ሊሰራ የታቀደው ሰፊ ስራ አቢሲንያ ባንክን የሳፋሪኮም ኤም ፔሳ ሱፐር ኤጀንት() እንዲሆን በማድረግ የተጀመረ ሲሆን ይኸውም አቢሲንያ ባንክ በሳፋ ኮም ኤም ፔሳ ሥር የተመዘገቡትን በርካታ ወኪሎችን የገንዘብ ዝውውር ሂደት እንዲያሳልጥ በተጨማሪም የአቢሲንያ ባንክ ደንበኞች የባንኩን የሞባይል መተግበሪያ(Mobile Application) እንዲሁም በዩኤስኤስዲ (*815#) በሳፋሪ ኮም 07 መስመር በመጠቀም ገንዘብ ከአቢሲንያ ባንክ ሂሳባቸው ወደ ኤም ፔሳ አካውንት እንዲሁም ከኤም ፔሳ ወደ አቢሲንያ ሂሳባቸው እንዲያስተላልፉ፣የተለያዩ የአገልግሎት ክፍያዎችን እንዲከፍሉ፣የሂሳብ መረጃቸውን እንዲያዩ ፣የአየር ሰዓት እንዲገዙና ሌሎችን የሞባይል ባንኪንግ አገልግሎቶች ከባንኩ እንዲያገኙ የሚያግዝ ነው፡፡
በስምምነቱ ላይ የሳፋኮም ኤም ፔሳ ጀነራል ማናጀር ሚስተር ፖል ካቫቩ እንደተናሩት “ከአቢሲንያ ባንክ ጋር በጋራ በመስራታችን ደስተኞች ነን፡፡ ተቋማችን ስራ ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ ከበርካታ ስትራቴጂካዊ አጋር ድርጅቶች ጋር በጋራ መስራት የጀመርን ሲሆን ከፋይናንስ ተቋማት ጋር መስራታችን የዲጂታል ክፍያ አማራጮችን ለደንበኞቻችን በመስጠት ረገድ ከፍተኛ ጠቀሜታ አለው፡፡ በተጨማሪም ደንበኞቻችን የአቢሲንያ ባንክ ቅርንጫፎችና የዲጂታል አገልግሎቶች በመጠቀም ወደዋሌታቸው እንዲሁም ከዋሌታቸው ገንዘብ ለማስተላለፍ ያስችላቸዋል ብለዋል፡፡”
“ከሳፋሪ ኮም ኤም ፔሳ ጋር የጋራ ስምምነት መፈራረማችን  ለደንበኞቻችን ተጨማሪ አገልግሎቶች ለማቅረብ የሚስችለን ነው፡፡ ዲጂታላይዜሽን የባንካችን ዋነኛ ስትራቴጂክ ምሰሶ በመሆኑ ለደንበኞቻችን የዲጂታል አገልግሎት ለመስጠት በምናደርገው ሂደት ላይ የራሱ አወንታዊ አስተዋፅኦ ይኖረዋል፡፡”ሲሉ የአቢሲንያ ባንክ ዋና የሪቴይል ባንኪንግ ኦፊሰር አቶ አብርሃም ገበየሁ በፊርማ ስነ ስርዐቱ ወቅት ተናግረዋል፡፡
ባንካችን ከሳፋሪ ኮም ኢትዮጵያ ጋር በበርካታ አገልግሎቶች ዙሪያ በጋራ እየሰራ እንደሚገኝ ይታወቃል፡፡
 
አቢሲንያ የሁሉም ምርጫ!

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Call Now Button