ደንበኞች የዲጂታል አማራጮችን በስፋት እንዲጠቀሙ የሚያበረታታው የባንካችን የ2ኛ ዙር የአቢሲንያ ቪዛ ካርድ የሽልማት ፕሮግራም የመጀመሪያ ሁለት ዕድለኞች ሽልማታቸውን ተቀበሉ።
ዛሬ ግንቦት 4 ቀን 2018 ዓ.ም በዋናው መ/ቤት አዳራሽ በተካሄደ ሥነ-ሥርዓት ላይ ይፋ እንደተደረገው የባንካችን የአፖሎ ዲጂታል ባንክ ደንበኛ የዘመናዊ ስልክ ሽልማት ሲቀበሉ የምስራቅ አዲስ ዲስትሪክት፣ ኮተቤ ወልገሞ ቅርንጫፍ ደንበኛ ደግሞ የ10,000 ብር የፕሪፔይድ ካርድ ሽልማት ዕድለኛ ሆነዋል።
የባንካችን ማርኬቲንግ ዳይሬክተር አቶ ተስፋዬ አበበ ዕድለኞቹን “እንኳን ደስ ያላችሁ!” በማለት ሽልማቱን ያበረከቱ ሲሆን፣ በቀጣይም ሌሎች ደንበኞች የባንካችንን የዲጂታል አማራጮች በመጠቀም ተሸላሚ እንዲሆኑ ጥሪ አቅርበዋል።
የባንካችንን 20 ደንበኞች የ2026 ፊፋ ዓለም ዋንጫን ለመታደም ዕድለኛ ያደረገው የመጀመሪያ ዙር የአቢሲንያ ቪዛ ካርድ የሽልማት ፕሮግራም አሁን በሁለተኛው ዙር ደግሞ ደንበኞች እንደ ግብይታቸው መጠን ፍሪጅ፣ ላፕቶፕ፣ ዘመናዊ ስልክ እና እስከ 10,000 ብር የሚደርስ የፕሪፔይድ ካርድ ተሸላሚ የሚሆኑበትን ዕድል ይዞ መጥቷል።








Leave a Reply