ባንካችን አቢሲንያ የተሟላ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት እየሰጠ በሚገኘው አቢሲንያ አሚን በኩል፤ የሴት ተማሪዎችን የትምህርት ጉዞ ለማቃናት ያለመ የድጋፍ መርሐ ግብር አከናወነ።
ባንኩ ተፈጥሯዊ ዑደትን ተከትሎ የሚመጣውን የትምህርት መስተጓጎል ለመቅረፍ ዛሬ ሚያዚያ 8 ቀን 2018 በሶስት የትምህርት ተቋማት በመገኘትና ከሐንስ ውመን ኬር ጋር በመተባበር ባደረገው የ 1.5 ሚሊዮን ብር ድጋፍ በድጋሚ ጥቅም ላይ የሚውል የንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁስ ማበርከት ችሏል።
“Keep Her at School / ከክፍሏ አትቅር” በሚል መሪ ቃል የተደረገው ይህ ድጋፍ፤ በአወሊያ፣ በተስፋ እና በአባድር ትምህርት ቤቶች ለሚማሩ 2,000 ሴት ተማሪዎች የተበረከተ ነው። ድጋፉ ተማሪዎቹ ያለምንም ስጋትና መደናቀፍ ትምህርታቸውን በትጋት እንዲከታተሉ ለማስቻል ታስቦ የተዘጋጀ ነው።
ይህንን የድጋፍ መርሐ-ግብር በትምህርት ቤቶቹ ተገኝተው ያስረከቡት የአቢሲንያ አሚን ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት ቺፍ ኦፊሰር አቶ አብዱልቃድር ሬድዋን ሲሆኑ፤ በዕለቱ የባንካችን ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችና የብራንድ አምባሳደሩ ተገኝተዋል።
አንዲትን ሴት ማስተማር ማኅበረሰብን ማስተማር እንደሆነ የሚያምነው ባንካችን፤ ማኅበራዊ ኃላፊነቱን በመወጣት የትውልድ አጋርነቱን በተግባር እያሳየ ይገኛል። ዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ ወገኖቻችንን መደገፍና ተማሪዎችን ማበረታታት የባንካችን አቢሲንያ አንዱ መገለጫ ተቋማዊ ዕሴት መሆኑ ይታወቃል።
አቢሲንያ የሁሉም ምርጫ!!










Leave a Reply