bankofabyssinia.com

ባንካችን አቢሲንያ በ7ኛው የታማኝ ግብር ከፋዮች የምስጋናና የዕውቅና መርሃ-ግብር ላይ የፕላቲኒየም ደረጃ ተሸላሚ ሆነ

· ባንካችን የዓመቱ የልዩ ሽልማት ተሸላሚም ሆኗል

ባንካችን አቢሲንያለ7ተኛ ጊዜ በተዘጋጀው የታማኝ ግብር ከፋዮች የምስጋናና የዕውቅና መርሃ-ግብር ላይ የፕላቲኒየም ደረጃ ሽልማት ተበርክቶለታል፡፡

መስከረም 27 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ማዕከል በተካሄደው ፕሮግራም ላይ በታክስ ህግ ተገዢነታቸውና በበጀት ዓመቱ ባበረከቱት የገቢ አስተዋጽኦ የላቀ አፈጻጸም ያስመዘገቡ 700 ተቋማት ሽልማታቸውንተቀብለዋል፡፡

በ2017 በጀት ዓመት የላቀ አፈጻጸም በማስመዝገባቸው በሃገር አቀፍ ደረጃ ዕውቅናና ሽልማት ከተሰጣቸው ከእነዚህ 700 ታማኝ ግብር ከፋዮች መካከል 105 በፕላቲኒየም ደረጃ ፣ 245 በወርቅ ደረጃ እና 350 ደግሞ በብር ደረጃ የተሸለሙ ናቸው፡፡

በተጨማሪም በተከታታይ ለ4 ዓመታት የፕላቲኒየም ደረጃ ተሸላሚ በመሆን ደረጃቸውን ጠብቀው በመገኘታቸው 30 ግብር ከፋዮች የዓመቱ የልዩ ሽልማት ተሸላሚ የሆኑ ሲሆኑ ባንካችን አቢሲንያም ከእነዚህ ተቋማት መካከል አንዱ በመሆን የልዩ ሽልማት ተሸላሚ ሆኗል፡፡

የአቢሲንያ ባንክ ዋና የፋይናንስ ኦፊሰር አቶ አብርሃም ገበየሁ የባንኩን የፕላቲኒየም ደረጃ እውቅናና ሽልማቱን ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር) ተቀብለዋል፡፡

በቀጣይም ባንካችን በዘመናዊ የባንክ ቴክኖሎጂ የታገዘ ቀልጣፋ አገልግሎት ለደንበኞቹ በማቅረብና ግብሩን በታማኝነት በመክፈል ለኢኮኖሚው እድገት የበኩሉን አስተዋጾ ማበርከቱን አጠናክሮ ይቀጥላል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Call Now Button