አቢሲንያ ባንክና ቪዛ ካርድ የ2021 የአፍሪካ ዋንጫ (AFCON 2021 Campaign) ጨዋታን ምክንያት በማድረግ በጋራ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጡ።

አቢሲንያ ባንክና ቪዛ ካርድ የ2021 የአፍሪካ ዋንጫ (AFCON 2021 Campaign) ጨዋታን ምክንያት በማድረግ በጋራ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጡ።

 የአቢሲንያ ቪዛ ካርድን ይጠቀሙ ፤ የቶታል ኢነርጂ የአፍሪካ ዋንጫ 2021 የጉዞ ዕድልን ያሸንፉ

 አዲስ አበባ፤ ኢትዮጵያ (ጥር 04 ቀን 2014 ዓ.ም)

በፈጣን የእድገት ግስጋሴ ላይ የሚገኘው አቢሲንያ ባንክ የ 2021 የአፍሪካ ዋንጫን ምክንያት በማድረግ በተዘጋጀው ፕሮግራም ( AFCON Campaign) ላይ የአቢሲንያ ቪዛ ካርድ ጠቀሜታዎች ለሃገራችን ገበያ ለማስተዋወቅ ከቪዛ ጋር ጥምረት መመስረቱን በታላቅ ደስታ ይገልፃል። ፕሮግራሙ በዋነኝነት የአቢሲንያ ቪዛ ካርድ ተጠቃሚዎች የአቢሲንያ ፖስ ማሽኖችን የበለጠ እንዲጠቀሙ በማበረታታት የቪዛ ካርድ ሽያጭንና አጠቃቀምን ለማሳደግ ታስቦ የተዘጋጀ ነው።

በዚህ ፕሮግራም አቢሲንያ ባንክና ቪዛ ካርድ ለሁለት የመጀመሪያ ደረጃ የሎተሪ ትኬት አሸናፊዎች ካሜሮን ላይ እየተካሄደ የሚገኘውን የ2021 የአፍሪካ ዋንጫ የፍፃሜ ጨዋታን ለመከታተል የሚያስችላቸውን ታላቅ ሽልማት ኣዘጋጅተዋል፡፡ ሽልማቱ እድለኞቹ በሀገሪቱ ባለ ታዋቂ ሆቴል የሁለት ቀን ወጪያቸውን ሸፍኖ እንዲሁም የዋንጫ ጨዋታውን በስታዲየሙ ተገኝተው በግለሰብ ደረጃ በተዘጋጀ የተለየ ስፍራ (VIP) ለመከታተል የሚያሰችል ዕድልን የሚያስገኝ ነው፤፤ በተጨማሪም በርካታ 42 ኢንች ቴሌቪዥኖችን፤ ስማርት የሞባይል ቀፎዎችን፤ ዲኮደሮችን ሌሎች ብዙ አጓጊ ስጦታዎች በሽልማቱ ተካተዋል።

ሌላው በፕሮግራሙ አቢሲንያ ባንክና ቪዛ ለአዲስ አበባ ነዋሪዎች የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን (ዋሊያዎቹ) የሚያደርጓቸውን ሁሉንም ጨዋታዎች በግሮቭ ጋርደን ዎክ  በነፃ እንዲከታተሉ ልዩ ዕድል ፈጥረዋል፤ፕሮግራሙ የተዘጋጀው ሁለቱ ተቋማት የአቢሲንያ ቪዛ ካርድ አጠቃቀም ላይ ከሚሰጡት የግንዛቤ ማስጨበጫ ጎን ለጎን የተለየ የመዝናኛ አጋጣሚን ለመፍጠር በማሰብ ነው።

በባንኩ የኦንላይን  ዳሬክተር የሆኑት አቶ አባይ ስሜ ፕሮግራሙን አስመልክተው፡፡ እስከዛሬ ድረስ የእግር ኳስ ጨዋታንና ባንካችንን በማስተሳሰር ደንበኞች ከ 1,000 በላይ በሚሆኑ የፖስ ማሽኖችን ሲጠቀሙ ማበረታቻ / ጉርሻ የሚሰጥ ዕድል የፈጠረ አጋጣሚ በፍፁም አልነበረም። ብሄራዊ ቡድናችን ከአመታት በኋላ እንደገና ወደ አፍሪካ ዋንጫ በመመለሱ ልባዊ ደስታ የተሰማን ሲሆን ዋልያዎቹ በቀሪዎቹ ጨዋታዎቻቸው መልካም እድል እንዲገጥማቸው እንመኛለን ብለዋል።

በኢትዮጵያ የተቋሙ (Visa) ዳይሬክተር አቶ አበበ ግርማይ በበኩላቸው ይህን በአይነቱ የመጀመሪያ የሆነውንና ለደንበኞቹ በርካታ ሽልማቶች ይዞ የመጣውን የአፍሪካ ዋንጫ ፕሮግራም (AFCON Campaign) ከአቢሲንያ ባንክ ጋር በጥምረት ለኢትዮጵያ ገበያ በማስተዋወቃችን ደስታችን ወደር የለውም ብለዋል፡፡

ቪዛ በተጨማሪ በአፍሪካ አህጉር ውስጥ ያሉ የእግር ኳስ ታዳሚያንን በፈጣን የክፍያ አውታር መረብ (Powerful payment) በማገኛኘት ለአፍሪካ እግር ኳስ አድናቂዎች ልዩና አይረሴ ትዝታዎችን ይፈጥራል።  ቪዛ የ2021 የቶታል ኢነርጂስ የአፍሪካ ዋንጫ የክብር (Official) ስፖንሰር ነው።

ጥቂት ቪዛን በተመለከተ፡-

ቪዛ (Visa Inc) በኤሌክትሮኒክስ (Digital) ክፍያ በዓለም ቀዳሚው ተቋም ነው፡፡ የድርጅቱ ዓላማ አለምን በዘመናዊ፣ አስተማማኝና ደህንነቱ በተጠበቀ የክፍያ ኔትወርክ  (መረብ) በማስተሳሰር የንግዱን ብሎም አጠቃላይ የኢኮኖሚውን ዕድገት ማፋጠን ነው፡፡ የተቋሙ እጅግ ዘመናዊ የሆነ አለምአቀፍ ኔትወርክ (VisaNet) ደህንነቱ የተጠበቀና ዘመናዊ ክፍያን በማከናወን በሴኮንድ 65‚000 የግብይት መልዕክቶችን መላክ የሚያስችል ነው፡፡

የቪዛ ዋነኛ ትኩረት የሆነው ፈጠራ ተቋሙ በየትኛውም ስፍራ ለሁሉም ሰው ከወረቀት ውጪ የሆነ ግብይትን  (Cashless Transaction) ለመፍጠር ለሚያደርገው ጥረት አንቀሳቃሽ ሞተር ነው፡፡ በአሁኑ ወቅት የምንኖርባት አለም በእጃችን ከምናከናውነው (Analog) ወደ ኤሌክትሮኒክ (Digital) የክፍያ ስርዓት  በምታደርገው ሽግግር ፣ ቪዛ ዘመናዊ ኔትወርኩን፣ የተለያዩ አገልግቶቹንና ባለሙያዎቹን በማቀናጀት  መጪውን  የንግድ ስርዓት መልሶ ቅርፅ ለማስያዝ ጠንክሮ ይሰራል፡፡ ለበለጠ መረጃ የተቋሙን ድረ ገጽ ይጎብኙ https://usa.visa.com/about-visa.html, https://usa.visa.com/visa-everywhere/blog.html

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Call Now Button