ኅዳር 22 ተጀምሮ እስከ ጥር 21፣ 2018 ዓ.ም ድረስ በሚቆየው “ከአቢሲንያ ባንክ ጋር ይጀምሩ – ያድሱ እና ይደጉ” በተሰኘው የሽልማት መርሃ-ግብር የ3ኛ ዙር ዕድለኞች ይፋ ሆነዋል።
ትናንት ጥር 12 ቀን 2018 ዓ.ም በዋናው መ/ቤት አዳራሽ የባንካችን ዴፒዩቲ ቺፍ ከስተመር ሪሌሽንሺፕና አክዊዜሽን ኦፊሰር የሆኑት አቶ ወሰንየለህ አበራ እና ሌሎች የባንካችን የስራ ሃላፊዎች እንዲሁም የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት ታዛቢዎች በተገኙበት የዕጣ አወጣጥ ሥነ-ሥርዓት ላይ ለዕጣ ዝግጁ ከነበሩ ከ 4.7 ሚሊዮን በላይ ዕጣዎች ውስጥ 5 ዕጣዎች ለዕድለኞች ወጥተዋል።
በዚህም መሠረት 2 የልብስ ማጠቢያ ማሽን የሚያስገኙት የ1ኛ ዕጣ ቁጥሮች 0294800517404 እና 0174700257754 በመሆን የወጡ ሲሆን፣ ሁለቱም በቅደም ተከተል በምስራቅ አዲስ እና ማዕከላዊ አዲስ ዲስትሪክት ስር ለሚገኙት ደጃዝማች ወንዲራድ እና ሰንጋ ተራ ቅርንጫፍ ደንበኞች ወጥተዋል።
እንዲሁም ብስክሌት የሚያስገኘው የ2ኛ ዕጣ ቁጥር 0265600639515 ሆኖ የወጣ ሲሆን የምዕራብ አዲስ ዲስትሪክት፣ ሸማ ተራ ቅርንጫፍ ደንበኛን ዕድለኛ አድርጓል።
በተመሳሳይ 2 ስማርት ስልኮችን የሚያስገኙት የ3ኛ ዕጣ ቁጥሮች ደግሞ 0657900176820 እና 0602800242154 ሆነው የወጡ ሲሆን፣ በቅደም ተከተል በምዕራብ አዲስ ዲስትሪክት ስር ለሚገኙት ለቡ ሴፍዌይ እና ዘነበወርቅ ቅርንጫፍ ደንበኞች ወጥተዋል።
ባንካችን ዕድለኞቹን ”እንኳን ደስ አላችሁ ! ” እያለ ሌሎች ደንበኞችም በዋናነት በፊት ገፅታ እና በጣት አሻራ የደንበኝነት ምዝገባ በማካሄድ እና በቅርንጫፍም ሆነ በዲጂታል አማራጮች የተለያዩ አገልግሎቶችን በመጠቀም ዘመናዊ ሃዩንዳይ ኤሰንት ሴዳን መኪናን ጨምሮ የሌሎች በርካታ ሽልማቶች አሸናፊ እንድትሆኑ ጥሪውን ያቀርባል።







Leave a Reply