አቢሲንያ ባንክ ህዳር 30 እና ታህሳስ 1 ቀን 2018 ዓ.ም በስካይ ላይት ሆቴል በተካሄደው ሁለተኛው የኢትዮጵያ የዲጂታል ባንኪንግ ጉባዔ ላይ ተሳተፈ።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዢ እዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) በጉባዔው ላይ አጽንኦት ሰጥተው እንደተናገሩት የዲጂታል ግብይት በሃገራችን የዕለት ተዕለት የንግድ እንቅስቃሴ ላይ ተጨባጭ ለውጥ አምጥቷል።
ብሔራዊ ባንክ በዚህ ጉባዔ ላይ የቀጣይ አምስት ዓመታት የብሔራዊ ዲጂታል ክፍያ ረቂቅ ስትራቴጂ ሰነድ ለተሰብሳቢዎች ይፋ ያደረገ ሲሆን በረቂቅ ሰነዱ ላይም የፓናል ውይይት ተካሂዷል።
በዚህ ጉባዔ ላይ ባንካችን መለያ ምልክቱን (Brand) እና የተለያዩ አገልግሎቶቹን የበለጠ ለማስተዋወቅ የቻለ ሲሆን፣ በሃገራችን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጉዞ ላይ ያለውን ሚናም ለማሳየት ችሏል።
በዚህ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ እና ኢትስዊች በጋራ ባዘጋጁት ጉባዔ ላይ ምክትል ጠ/ሚ ተመስገን ጥሩነህን ጨምሮ ከባንኮች፣ ከኢትዮ ቴሌኮም እና ከተለያዩ የዲጂታል ክፍያ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት የተወከሉ ግለሰቦች ተሳትፈዋል።






Leave a Reply