አቢሲንያ ባንከ በተጠናቀቀው የ2020/21 በጀት ዓመት በሁሉም ዋና ዋና መሪ ዕቅድ አፈጻጸም አንጻር፤ በተለይም በተቀማጭ ገንዘብ ማሰባሰብ፣ የውጪ ምንዛሬ ግኝትና የብድር ስርጭት ከዕቅዱና ከመቼውም ጊዜ በላይ የላቀ አፈጻጸም አስመዝግቧል፡፡ በበጀት ዓመቱ የብር 41.26 ቢልዮን ተጨማሪ የተቀማጭ ገንዘብ በማሰባሰብ በተመሳሳይ በጀት ዓመት በባንክ ኢንዱስትሪው በግል ባንኮች ከተሰበሰበው ተጨማሪ የተቀማጭ ገንዘብ /Incremental Deposit/ አንጻር መሪ ያደረገውን ውጤት ማስመዘገብ ችሏል፡፡ እንደዚሁም ከ2.5 ሚሊዮን በላይ አዳዲስ ደንበኞችን በመመልመል ሂሳብ እንዲከፍቱ ከማድረጉም በተጨማሪ የላቀ ቁጥር ያላቸው ደንበኞቹን የካርድ፣ የሞባይልና የኢንተርኔት ባንኪንግ አገልግሎት ተጠቃሚዎች ማድረግ ችሏል፡፡ ባንካችን ከታክስና ከሕጋዊ ተጠባባቂ ሂሳብ በፊት የብር 2.87 ትርፍ በማስመዝገብ ከዕቅዱ በላይ እጅግ ከፍተኛ ውጤት በማምጣት የበጀት ዓመቱን አጠናቅቋል፡፡
Bank of Abyssinia has achieved huge success in terms of profit, deposit collection, foreign exchange earnings, and loan disbursements during the 2020/21 fiscal year. Accordingly, the bank earned a huge profit of Birr 2.87 Billion before tax which is a record high in the bank’s history. Besides, it has collected Birr 41.26 billion incremental deposits, which is significantly higher than the incremental deposit rate of all private Banks. Additionally, more than 2.5 million new customers have been recruited. A large number of card, mobile, and Internet banking services have been launched during this fiscal year as well.
Leave a Reply