የአቢሲንያ ባንክ አ.ማ አክሲዮኖች በማዕከላዊ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ግምጃ ቤት (Central Security Depository) ላይ የተመዘገቡ መሆኑን ስለማሳወቅ

የአቢሲንያ ባንክ አ.ማ አክሲዮኖች በማዕከላዊ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ግምጃ ቤት (Central Security Depository) ላይ የተመዘገቡ መሆኑን ስለማሳወቅ

አቢሲንያ ባንክ አ.ማ ሁሉንም አክሲዮኖች በኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለሥልጣን (ECMA) እና በማዕከላዊ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ግምጃ ቤት (CSD) በኩል የወጡ መመሪያዎችና አግባብነት ባላቸው ሕጎች መሠረት አክሲዮኖቹ በኤሌክትሮኒክ መልክ በተሳካ ሁኔታ በማዕከላዊ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ግምጃ ቤት (CSD) ላይ መመዝገባቸውን እንዲሁም በምዝገባው ሂደት ወደ ግምጃ ቤት (CSD) ገቢ የተደረጉ የባለአክሲዮኖች መረጃዎችና የአክሲዮን ድርሻ ትክክለኛ ስለመሆናቸው ባንካችን ለግምጃ ቤቱ ማረጋገጫ የሰጠ መሆኑን እያሳወቅን የሚከተሉትን ነጥቦች በሕጉ መሠረት ባንኩ ለባለአክሲዮኖች በሙሉ እና ለህዝብ የማሳወቅ ግዴታ ስላለበት እንደሚከተለው እናሳውቃለን፡፡

  1. በግምጃ ቤት ምዝገባ ከተጠናቀቀበት እ.አ.አ ማርች 17, 2026 (ከመጋቢት 08 ቀን 2018 ዓ.ም) ጀምሮ በአቢሲንያ ባንክ አ.ማ በህግ ተቀባይነት ያለው የአክሲዮን ባለቤትነት መብት የሚረጋገጠው በማዕከላዊ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ግምጃ ቤት (CSD) ሲስተም ተገቢው ምዝገባ ሲከናወንና የግዑዝ አልባ የአክሲዮን ባለቤትነት መብት ሲጠናቀቅ ይሆናል፡፡
  2. ከዚህ በኋላ በወረቀት መልክ የተዘጋጁም ሆኑ የተሰጡ የአክሲዮን ሠርተፍኬቶች የአክሲዮን ባለቤትነትን፣ የአክሲዮን ዝውውርን፣ በአክሲዮን ላይ የተደረገ የመያዣ መብት እና ሌሎች በአክሲዮኖች ላይ የሚደረጉ ግብይቶችን ለማስረዳት በህግ ተቀባይነት ያለው ማስረጃ ሆነው አያገለግሉም፡፡
  3. ሁሉም በአክሲዮኖች ላይ የሚፈጠሩ የባለቤትነት መብቶች፣ የአክሲዮን ዝውውሮች፣ መያዣዎች እና አነዚህን የሚመለከቱ የኩባንያው ውሳኔዎች ህጋዊ እውቅና የሚያገኙት አግባብነት ባላቸው የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለሥልጣን (ECMA) መሠረት በማዕከላዊ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ግምጃ ቤት (CSD) ሲስተም ሲመዘገቡ ብቻ ይሆናል፡፡ በዚሁ መሠረት፡-
    1. ባለአክሲዮኖች ከዚህ በፊት የተረከባችሁትን የአክሲዮን ሰርተፊኬቶች በተመለከተ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ግምጃ ቤት (CSD) አባል ከሆኑት መካከል በመረጣችሁት ተቋም የሰነደ ሙዋለ ንዋይ የግብይት ሂሳብ (Securities Trading Account) በመክፈት ሰርተፊኬቶቻችሁን እንድታስረክቡ፡፡
    1. የባንኩን የወረቀት የአክሲዮን ሰርተፍኬቶችን ለፋይናንስ ተቋማት፣ ሌሎች መያዣ ተቀባዮች ወይም ለግለሰቦች በዋስትና ያስያዛችሁ ባለአክሲዮኖች የወረቀት የአክሲዮን ሰርተፊኬቶች ቀሪ የተደረጉ በመሆኑ፤ በአክሲዮኖቹ ላይ ያቋቋማችሁት የመያዣ መብት የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ግምጃ ቤት (CSD) ሲስተም እንዲመዘገብ፣ ሰርተፊኬቶቹን በተ.ቁ. 3.1 ከተጠቀሱት የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ግምጃ ቤት (CSD) አባል ከሆኑት ተቋማት መካከል በመረጣችሁት ተቋም በመቅረብ ሰነዶቹን ተመላሽ እንድታደርጉ እየገለጽን፤
    1. ባለአክሲዮኖችና የሚመለከታቸው መያዣ ተቀባዮች ከዚህ በላይ በተጠቀሰው መሠረት የሰነድ አክሲዮን ሰርተፊኬቶችን በማስረከብ ወደ ግዑዝ ዓልባ እንዲቀይሩ እያሳሰብን፤ ይህን እስኪያጠናቅቁ ድረስ የአክሲዮን የማስተላለፍ፣ የማስያዝና በአክሲዮኖቻቸው ላይ ማንኛውንም ዓይነት መብት ለመጠቀም ሊቸገሩ እንደሚችሉ እናሳስባለን፡፡  
    1. ከዚህ በኋላ የአክሲዮን ቅድሚያ የመግዛት መብት (Right Issues) መጠቀም፣ የቦነስ አክሲዮን ድልድል፣ እና ሌሎች የአክሲዮን የሚመለከቱ ውሳኔዎች ተፈፃሚ የሚሆኑት በሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ግምጃ ቤት (CSD) ሲስተም ይሆናል፡፡

ተጨማሪ ማብራሪያ የምትፈልጉ ባለአክሲዮኖች በአቢሲንያ ባንክ ዋናው መሥሪያ ቤት አክሲዮን እና ኢንቨስትመንት በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 0115-526314 ላይ በመደወል መረጃ ማግኘት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

ይህ ማስታወቂያ ለባንኩ ባለአክሲዮኖች በሙሉና ለሚመለከታቸው በሙሉ በባንኩ የተላለፈ ነው፡፡  

አቢሲንያ ባንክ አ.ማ.

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Call Now Button