ባንካችን አቢሲንያ በዛሬው ዕለት 680ኛ የሆነውን ቅርንጫፉን በአፍሪካ ሕብረት ቅፅር ግቢ ውስጥ አስመርቆ ሥራ አስጀመረ!

ባንካችን አቢሲንያ በዛሬው ዕለት 680ኛ የሆነውን ቅርንጫፉን በአፍሪካ ሕብረት ቅፅር ግቢ ውስጥ አስመርቆ ሥራ አስጀመረ!

ባንካችን አቢሲንያ ከቀዳሚዎቹ የግል ባንኮች ተርታ የሚሰለፍ ሲሆን፣ ዛሬ ይፋዊ የምርቃት ሥነ-ሥርዓት የተከናወነለት የአፍሪካ ዩኒየን ኮምፓውንድ ቅርንጫፍ የባንካችን 680ኛ ቅርንጫፍ በመሆን ሙሉ የባንክ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል፡፡ 

እ.ኤ.አ. በ2030 በምሥራቅ አፍሪካ ቀዳሚ ባንክ የመሆን ርዕዩን ሰንቆ በከፍተኛ የሥራ ተነሳሽነት እየሠራ የሚገኘው ባንካችን አቢሲንያ ስኬታማ የሆነ የእቅድ ዘመን እያሳለፈ ይገኛል፡፡ የባንካችንም መሪ ቃል ‹‹የሁሉም ምርጫ›› እንደ መሆኑ በዚህ ቅፅር ለሚገኙ አፍሪካዊ ወንድሞቻችንና እና እህቶቻችን ልባዊ አገልግሎት ለመስጠት ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ዝግጁ ሆነናል፡፡

ባንካችን አቢሲንያ በተለያየ መስክ ለሀገራችን ኢትዮጵያ ብሎም ለአፍሪካ ባለውለታ በሆኑ ጀግኖች ስም ቅርንጫፎች እንዲሰየሙ በማድረግ ስማቸውና ታሪካቸው እንዳይረሳና እንዲዘከር ሲያደርግ ቆይቷል፡፡

ከነዚህም ባለውለታዎች መካከል በግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዘመን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርና ጠቅላይ ሚኒስቴር በመሆን ባገለገሉት፣ የተባበሩት መንግሥታት ቻርተርን በማርቀቅና ሀገራችን ኢትዮጵያ መስራች አባል እንድትሆን ከፍተኛ አስተዋጽኦ ባደረጉት እና የአፍሪካ አንድነት ድርጅትን በከፍተኛ ውጣ ውረድ በማቋቋም ጽ/ቤቱ አዲስ አበባ እንዲሆን ከፍተኛ ተጋድሎ ባደረጉት ፀሐፊ ትዕዛዝ አክሊሉ ሀብተወልድ ስም ባንካችን ቅርንጫፉን አክብሮ ሰይሟል፡፡ እንዲሁም ታላቁ አፍሪካዊ የስፖርት ሰው ክቡር አቶ ይድነቃቸው ተሰማም ሌላው ባንካችን ቅርንጫፉን አክብሮ ከሰየመላቸው የኢትዮጵያ ብሎም የአፍሪካ ባለውለታዎች መካከል ተጠቃሾቹ ናቸው፡

ባንካችን ለደንበኞቹ ምቾቱን የጠበቀና የላቀ የባንክ አገልግሎት ለመስጠት ሲባል ለዲጂታል ቴክኖሎጂ (Digitalization) ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቷል፡፡ በዚህም መሠረት የሞባይል ባንኪንግ፣ ኢንተርኔት ባንኪንግ፣ አቢሲንያ ኦንላየን፣ ኢ-ኮሜርስ ፔይመንት ጌትዌይ፣ ቨርችዋል ባንኪንግ፣ ያሉ የኦንላየን የባንክ አገልግሎቶችን በመጀመር እንዲሁም የኤ.ቲ.ኤምና የፖስ መሣሪያ በማኅበረሰባችን ዘንድ ይበልጥ ተደራሽ በማድረግ፣ ዓይነ ስውራን ደንበኞቹን ማዕከል ባደረገ መልኩም የተለያዩ የባንክ አገልግሎቶችን ለማግኘት የሚያስችላቸውን በድምጽ የታገዘ የኤ.ቲ.ኤም. የባንክ አገልግሎት ተግባራዊ በማድረግ ከፍተኛ ሥራ በመሥራት ላይ ይገኛል፡፡

በመጨረሻም በቅርንጫፉ የአይቲኤም (Virtual Banking Service) አገልግሎት ሙሉ በሙሉ የሚሰጥ መሆኑን ስናሳውቅ በደስታ ነው፤፤

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Call Now Button