ባንካችን አቢሲንያ ለዳግማዊ ምኒልክ ሪፈራል ሆስፒታል የዲያሊስስ ሕክምና ማዕከል እና የቀድሞ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ለነበሩት ለአቶ ዱባለ ጃሌ ድጋፍ አደረገ!

ባንካችን አቢሲንያ ለዳግማዊ ምኒልክ ሪፈራል ሆስፒታል የዲያሊስስ ሕክምና ማዕከል እና የቀድሞ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ለነበሩት ለአቶ ዱባለ ጃሌ ድጋፍ አደረገ!

ባንካችን አቢሲንያ ለዳግማዊ ምኒልክ ሪፈራል ሆስፒታል የዲያሊስስ ሕክምና ማዕከል እና የቀድሞ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ለነበሩት ለአቶ ዱባለ ጃሌ ድጋፍ አደረገ!//ሁለት የኩላሊት እጥበት ማከናወኛ እንዲሁም ሌሎች አራት ተያያዥ የሕክምና መስጫ መሣሪያዎችን የባንካችን ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ በቃሉ ዘለቀ ለዳግማዊ ሚኒሊክ ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ዋና ሥራ አስፈፃሚ ለሆኑት ዶ/ር ታደሠ ኃብተዮሐንስ፣ በዛሬው ዕለት ሃያት ሬጀነሲ ሆቴል በተካሄደ ሥነ ስርዓት ላይ አበርክተዋል፡፡በዚህ ርክክብ ሥነ ሰርዓት ላይ ተቋሙን በመወከል ንግግር ያደረጉት ዶ/ር ታደሠ፣ ይህ ልገሳ ትልቅ ችግር የሚፈታ እንዲሁም ለቅድመ መከላከል ዝግጅት ለሆስፒታሉ እንዲሁም ለታካሚዎች ጉልህ አስተዋፆ እንደሚያደርግ አብራርተው ተቋሙን በመወከል ለባንኩ ከፍተኛ ምስጋና አቅርበዋል፡፡ይህ በእንዲህ እንዳለ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ 7ተኛው ገዢ በመሆን እ.ኤ.አ. ከ1995 እስከ 2006 ለአስራ አንድ ዓመታት ባንኩን እና የባንኩን ኢንዱስትሪ ያገለገሉት አቶ ዱባለ ጃሌ አንዱ መሆናቸው ይታወሳል፡፡በኢትዮጵያ የባንክ ኢንዱስትሪ ውስጥ የራሳቸው የሆነ ደማቅ አሻራ ያሳረፉት እኚህ አንጋፋ ሰው ከፍተኛ በሆነ የኩላሊት ሕመም እየተቸገሩ እንዳለ ባንካችን ተረድቶ፣ ለእኚህ አንጋፋ የሀገር ባለውለታ ለሕክምና ወጪያቸው ይረዳቸው ዘንድ የብር 1,000,000 (አንድ ሚሊዮን) ድጋፍ በባንካችን ዋና ሥራ አስፈፃሚ በተገኙበት ተበርክቶላቸዋል፡፡አቶ ዱባለ ጃሌም ለተደረገላቸው ከፍተኛ ድጋፍ ባንኩን እንዲሁም መላውን የባንኩን ሠራተኞች አመስግነዋል፡፡ባንካችን ለሀገር ባለውለታዎቻችን በስማቸው ቅርንጫፍ በመክፈት ታሪካቸው ለልጅ ልጅ እንዲተላለፍ፣ ታሪካቸው ተሰንዶ እንዲቀመጥ በማድረግ እና በሌሎችም ተግባራት የበኩልን ድርሻ ከማለዳው ጀምሮ ሲወጣ ቆይቷል፡፡ከዚሁ ጎን ለጎን ባንካችን አቢሲንያ የሁሉም ኢትዮጵያዊ ባንክ፣ የሁሉም ምርጫ እንደ መሆኑ ከመንግሥት፣ ከግብረ ሠናይ ድርጅቶች እና ከግለሰቦች ለሚቀርቡለት የድጋፍ ጥያቄዎች በጎ ምላሽ በመስጠት ማኅበራዊ ኃላፊነቱን በሚገባ ሲወጣ ቆይቷል፡፡ ባንካችን ባሳለፍነው አንድ ዓመት ውስጥ ለተለያዩ የድጋፍ ጥያቄዎች ከብር 66 ሚሊዮን በላይ ድጋፍ አድርጓል፡፡ ለፌደራል መንግሥት፣ በክልል መስተዳደሮች እና በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለቀረቡለት የተለያዩ የድጋፍ ጥያቄዎች፣ በኮቪድ 19 ወረርሺኝ ምክንያት ለተፈጠሩ ማኅበራዊ ችግሮች ባንካችን የበኩሉን ሰፊ አስተዋጽኦ አድርጓል፡፡683 በሚደርሱ ቅርንጫፎች፣ ከ105 ቢሊዮን ብር በላይ የተቀማጭ ገንዘብ፣ እንደ ቨርቹዋል የባንክ አገልግሎት ያሉ አዳዲስ የባንክ ቴክኖሎጂዎችን ለባንክ ኢንዱስትሪው ብሎም ለሀገራችን እያስተዋወቀ ያለው ባንካችን አቢሲንያ የሀገር የወገን አለኝታነቱን በቀጣይም አጠናክሮ ይቀጥላል፡፡ማህበራዊ ኃላፊነትን መወጣት ዕሴታችን ነው!

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Call Now Button