ንካችን አቢሲንያ በጋራ ለመሥራት ፍላጎት ካሳዩ ኤጀንሲዎች መካከል አንዱ ከሆነውና በስሩ በርካታ አባላትን ካቀፈው “ፊውቸር ኢትዮ” (Future Ethio) የውጭ ሃገር የሥራ ስምሪት ኤጀንሲዎች ማኅበር አባላት ጋር ውይይት አካሄደ።
ጥር 22 ቀን 2018 ዓ.ም በዋናው መ/ቤት በተካሄደው ውይይት በተለይም የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ባወጣው አዲስ መመሪያ መሠረት ወደ ውጭ ሃገር ሠራተኞችን የሚልኩ ኤጀንሲዎች ፈቃዳቸውን እንዲያድሱ በተሰጠው አቅጣጫ ዙሪያ የሃሳብ ልውውጥ ተደርጓል።
በውይይቱ ላይ የተገኙት የባንካችን የስራ ሃላፊዎችም ከማኅበሩ አባላት ጋር በዘላቂነት በጋራ መሥራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ የመከሩ ሲሆን፣ ከተሳታፊዎች ለተነሱ ጥያቄዎችም ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል።
ለኤጀንሲዎቹ የቀረቡ አገልግሎቶችን በተመለከተም የሥራ ዋስትና ብድር (Guarantee) አቅርቦትን እና የሥራ ማስኬጃ ካፒታል (Working Capital) በተመለከተ ዝርዝር ገለጻ ተደርጓል።
ለሠራተኞች ከሚቀርቡ ጥቅሞች ጋር በተገናኘም ኤጀንሲዎቹ ወደ ውጭ ለሚልኳቸው ሠራተኞች የሚሰጥ የሞባይል ቀፎ (Device Financing) ብድር እና ሠራተኞቹ ወደ ሃገራቸው ሲመለሱ የሚቋቋሙባቸው ልዩ ልዩ የብድር ዓይነቶች እንደቀረቡ ተነግሯል።
በመጨረሻም ውይይቱ በጋራ ለመሥራት የሚያስችል መግባባት ላይ በመድረስ በስኬት ተጠናቅቋል።








Leave a Reply