ባንካችን አቢሲንያ ታህሣሥ 16 ቀን 2018 ዓ.ም ለአ.አ.ዩ የአካል ጉዳተኛ ተማሪዎች የሚውል ወደ ብር 400,000 የሚጠጋ ድጋፍ አበረከተ።
ባንካችን ይህን ድጋፍ ያበረከተው አ.አ.ዩ “አካል ጉዳተኝነትን የሚያካትት ማህበረሰብ መገንባት ለተሻለ ማህበራዊ ዕድገት!” በሚል መሪ ሀሳብ የዘንድሮውን የአካል ጉዳተኞች ቀን በዩኒቨርስቲው ቅጥር ጊቢ ባከበረበት ወቅት ነው።
በአይነት የቀረበው ይህ ለአካል ጉዳተኞች የሚውል የመማሪያና ለእንቅስቃሴ የሚረዱ ቁሳቁሶችን ያካተተውን ድጋፍ የባንካችን የኮርፖሬት ኮምዩኒኬሽንስ ስ/አስኪያጅ የሆኑት ወ/ሮ ኤልሳቤጥ ገብሩ አስረክበዋል።
ወ/ሮ ኤልሳቤጥ ድጋፉን ካስረከቡ በኋላ እንደተናገሩት ይህ ድጋፍ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የአካል ጉዳተኛ ተማሪዎችን አካታችነት በብዙዎች ዘንድ እንዲታወቅና የመማር ማስተማሩ ለሁሉም አመቺ እንዲሆን እያደረገ ላለው ከፍተኛ ጥረት ዕውቅና ለመስጠት የተደረገ ነው ብለዋል።
የአ.አ.ዩ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ በበኩላቸው አቢሲንያ ባንክ በቀናነት ላደረገላቸው ድጋፍ አመስግነው በቀጣይ ምባንኩ ከጎናቸው እንደሚሆን እምነታቸው እንደሆነ በአጽንኦት ገልጸዋል። ባንካችን እያደረገ ላለው ድጋፍም ዩኒቨርስቲው የእውቅና የምስክር ወረቀት አበርክቶለታል።
የኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች ማህበራት ፌዴሬሽን ዋና ዳይሬክተር የሆኑት አቶ አባይነህ ጉጆ በበኩላቸው አቢሲንያ ባንክ ስሙ ብዙውን ጊዜ በመሰል በጎ አድራጎት ተግባራት ላይ የሚነሳ እንደሆነተናግረው፣ ሌሎች መሰል ተቋማትም የባንኩን አርአያ እንዲከተሉ ጥሪ አቅርበዋል።
በክብረ በዓሉ ላይ የዩኒቨርስቲውን ፕሬዝዳንት ጨምሮ መላው የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ፣ አርቲስቶች ፤ ተማሪዎች እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።












Leave a Reply