የተከበራችሁ የአቢሲንያ ባንክ አ.ማ. ባአክሲዮኖች
በኢትዮጵያ ንግድ ሕግ አንቀጽ 366(1)፣ 367(1) እና አንቀጽ 370 እንዲሁም በአክሲዮን ማህበሩ የተሻሻለው የመመሥረቻ ጽሑፍ አንቀጽ 20 መሠረት የአቢሲንያ ባንክ አ.ማ. የባለአክሲዮኖች 29ኛ መደበኛ እና 16ኛ አስቸኳይ ጉባዔዎች ማክሰኞ መስከረም 20 ቀን 2018 ዓ.ም. ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት ጀምሮ አዲስ አበባ ከተማ ፒያሳ አካባቢ በሚገኘው የአድዋ ድል መታሰቢያ የፓን አፍሪካ አዳራሽ ስለሚካሄድ ባለአክሲዮኖች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በጠቅላላ ጉባዔዎቹ ላይ እንድትገኙ የባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡
የአክሲዮን ማህበሩ ዋና መ/ቤት አድራሻ፡- አዲስ አበባ፣ ቂርቆስ ክ/ከተማ፣ ወረዳ 07፣ የቤ/ቁ. 351/1 | የአክሲዮን ማህበሩ የምዝገባ ቁጥር KK/AA/2/0001775/2004የአክሲዮን ማህበሩ ዓይነት፡- በባንክ ሥራ ላይ የተሠማራ |
የባንኩ ድረ-ገጽ፡- https://www.bankofabyssinia.com | አክሲዮን ማህበሩ የተፈረመ ዋና ገንዘብ፡- 15,000,000,000 |
የአክሲዮን ማህበሩ ስም፡- አቢሲንያ ባንክ አ.ማ. | አክሲዮን ማህበሩ የተከፈለ ዋና ገንዘብ፡- 15,000,000,000 |
1. የ29ኛው ዓመታዊ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ አጀንዳዎች
1.1. አዳዲስ ባለአክሲዮኖችን መቀበልና የተደረጉ የአክሲዮን ዝውውሮችን ማሳወቅ፣
1.2. የዳይሬክተሮች ቦርድን እ.ኤ.አ. የ2024/2025 የሒሳብ ዓመት ዓመታዊ ሪፖርት ማዳመጥ፣
1.3. የውጭ ኦዲተሮችን እ.ኤ.አ. የ2024/2025 የሒሳብ ዓመት ሪፖርት ማዳመጥ፣
1.4. በተራ ቁጥር 1.2 ላይ በቀረበው የዳይሬክተሮች ቦርድ ሪፖርት ላይ ተወያይቶ መወሰን፣
1.5. በተራ ቁጥር 1.3 ላይ በቀረበው የውጭ ኦዲተሮች ሪፖርት ላይ ተወያይቶ መወሰን፣
1.6. እ.ኤ.አ. በ2024/2025 የሒሳብ ዓመት የተጣራ ትርፍ አደላደልና አከፋፈል ላይ ውሳኔ መስጠት፣
1.7. እ.ኤ.አ. ከ2025/2026 እስከ 2028/2029 የሒሳብ ዓመት የውጭ ኦዲተር መሾምና የአገልግሎት ክፍያውን መወሰን፣
1.8. እ.ኤ.አ. የ2024/2025 ሒሳብ ዓመት የዳይሬክተሮች ቦርድ ዓመታዊ የሥራ ዋጋ ክፍያን መወሰን፣
1.9. እ.ኤ.አ. የ2025/2026 ሒሳብ ዓመት የዳይሬክተሮች ቦርድ ወርሃዊ የአበል ክፍያ መወሰን፣
1.10. የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት ምልመላና ምርጫ ማስፈፀሚያ የአሠራር ደንብ ረቂቅ ላይ ተወያይቶ ማጽደቅ፣ (ረቂቅ ደንቡን ከባንኩ ድረ-ገጽ ላይ ማግኘት ይቻላል፡፡)
2. የ16ኛው አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ አጀንዳዎች
2.1. የባንኩን ካፒታል ለማሳደግ በዳይሬክተሮች ቦርድ በሚቀርበው የውሳኔ ሃሳብ ላይ ተወያይቶ መወሰን፣
2.2. የባንኩን የመመሥረቻ ጽሑፍ ማሻሻል፣
3. ማሳሰቢያ
3.1. በጉባዔው መገኘት የማይችሉ ባለአክሲዮኖች ተወካዮቻቸው ሥልጣን ባለው የመንግሥት አካል ተረጋግጦ የተሰጠ የውክልና ሠነድ ዋናውና ፎቶኮፒ በመያዝ ወይም በንግድ ሕግ አንቀጽ 377 መሠረት ጉባዔው ከመካሄዱ ከ3 የሥራ ቀናት በፊት ለገሃር በሚገኘው የባንኩ ዋና መ/ቤት 8ኛ ፎቅ አክሲዮንና ኢንቨስትመንት ክፍል ለዚሁ ዓላማ በማህበሩ የተዘጋጀውን የውክልና ቅጽ ሞልተው በመፈረም ተወካይ መሾምና ተወካዩም የውክልና ማስረጃውን በመያዝ የጉባዔው ተካፋይ ለመሆንና ድምጽ ለመስጠት የሚችሉ መሆኑን በአክብሮት እንገልጻለን፡፡ ሆኖም አንድ ባለአክሲዮን በማህበሩ ጠቅላላ ጉባዔ በማናቸውም ችሎታ መወከል የሚችለው አንድ ሰው ብቻ መሆኑን፣ እንዲሁም የባንኩ ሠራተኞች ለባለአክሲዮኖች ወኪል በመሆን በጉባዔዎቹ ላይ መሳተፍ የማይችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
3.2. የአክሲዮን ማህበሩ ባለአክሲዮኖች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በጉባዔው ላይ ለመሳተፍ ሲመጡ በኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ አዋጅ ላይ በተደነገገው መሠረት ተገቢውን መረጃ ለማሟላት እንዲረዳ የኢትዮጵያ ዲጂታል መታወቂያ ካርድ (ፋይዳ) ዋናውና ኮፒውን በመያዝ መሳተፍ የሚችሉ መሆኑን በአክብሮት እናሳውቃለን፡፡
የአቢሲንያ ባንክ አ.ማ. የዳይሬክተሮች ቦርድ
Leave a Reply