bankofabyssinia.com

የባንካችን “ከአቢሲንያ ባንክ ጋር ይጀምሩ – ያድሱ እና ይደጉ” የሽልማት መርሃ-ግብር 2ኛ ዙር ዕድለኞች ይፋ ሆኑ

የባንካችን “ከአቢሲንያ ባንክ ጋር ይጀምሩ – ያድሱ እና ይደጉ” የሽልማት መርሃ-ግብር 2ኛ ዙር ዕድለኞች ይፋ ሆኑ

ከኅዳር 22 – ጥር 21፣ 2018 ዓ.ም ድረስ እየተካሄደ በሚገኘውና “ከአቢሲንያ ባንክ ጋር ይጀምሩ – ያድሱ እና ይደጉ” በተሰኘው የሽልማት መርሃ-ግብር የ2ኛ ዙር ዕድለኞች ይፋ ሆነዋል።

ትናንት ታህሳስ 21 ቀን 2018 ዓ.ም በዋናው መ/ቤት አዳራሽ የባንካችን ከስተመር ማኔጅመንት ቺፍ ኦፊሰር አቶ ደሳለኝ ይዘንጋው እና ሌሎች የባንካችን የስራ ሃላፊዎች እንዲሁም የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት ታዛቢዎች በተገኙበት የዕጣ አወጣጥ ሥነ-ሥርዓት ላይ ለዕጣ ዝግጁ ከነበሩ ከ 3 ሚሊዮን በላይ ዕጣዎች ውስጥ 5 ዕጣዎች ለዕድለኞች ወጥተዋል።

በዚህም መሠረት ፍሪጅ የሚያስገኘው የ1ኛ የዕጣ ቁጥር 0195200840327 ሆኖ የወጣ ሲሆን የባህር ዳር ዲስትሪክት፣ አቸፈር ቅርንጫፍ ደንበኛን ዕድለኛ አድርጓል።

እንዲሁም 2 ብስክሌቶችን የሚያስገኙት የ2ኛ ዕጣ ቁጥሮች ደግሞ 064590037 እና 0332700431174 በመሆን የወጡ ሲሆን ሁለቱም በቅደም ተከተል በምስራቅ አዲስ አበባ ዲስትሪክት ስር ለሚገኙት የቦሌ አራብሳ እና ሞላሌ ቅርንጫፍ ዕድለኞች ወጥተዋል።

በተመሳሳይ 2 ስማርት ስልኮችን የሚያስገኙት የ3ኛ ዕጣ ቁጥሮች ደግሞ  0017400819451 እና 0126500479715 ሆነው የወጡ ሲሆን፣ በቅደም ተከተል በመካከለኛው ዲስትሪክት ስር ለሚገኘው አራዳ ቅርንጫፍ እና በምስራቅ አዲስ አበባ ዲስትሪክት ስር ለሚገኘው ጉርድ ሾላ ቅርንጫፍ ደንበኞች  ወጥተዋል።

ባንካችን ዕድለኞችን ”እንኳን ደስ አላችሁ ! ” እያለ ሌሎች ደንበኞችም በዋናነት በፊት ገፅታ እና በጣት አሻራ የደንበኝነት ምዝገባ በማካሄድ እና በቅርንጫፍም ሆነ በዲጂታል አማራጮች ሌሎች አገልግሎቶችን በመጠቀም ዘመናዊ ሃዩንዳይ ኤሰንት ሴዳን መኪናን ጨምሮ የሌሎች በርካታ ሽልማቶች አሸናፊ እንድትሆኑ ጥሪ እያቀረበ ባሳለፍነው ሳምንት ዕድለኛ የነበሩ 9 ደንበኞቻችንን በዚሁ ገጽ ይፋ የምናደርግ መሆኑን እንገልፃለን።

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Call Now Button