ባንካችን አቢሲንያ እና ቪዛ የ2026 ፊፋ ዓለም ዋንጫን ለመታደም ዕጣ የወጣላቸዉን የመጀመሪያ ዙር 4 ዕድለኞች ይፋ አደረጉ

ባንካችን አቢሲንያ እና ቪዛ የ2026 ፊፋ ዓለም ዋንጫን ለመታደም ዕጣ የወጣላቸዉን የመጀመሪያ ዙር 4 ዕድለኞች ይፋ አደረጉ

ባንካችን አቢሲንያ እና ቪዛ ደንበኞችን ለማበረታታት ብሎም ለመሸለም የ2026 ፊፋ ዓለም ዋንጫን ለመታደም የሚያስችል ዕጣ የወጣላቸዉን የመጀመሪያ ዙር 4 ዕድለኞች በጋራ ይፋ አደረጉ።

መጋቢት 8 ቀን 2018 ዓ.ም በዋናው መ/ቤት የባንካችን የሥራ ሐላፊዎችና የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት ታዛቢዎች በተገኙበት መርሐ ግብር ላይ የባንካችን የዲጂታል ከስተመር አኪዩዜሽን ዳይሬክተር አቶ አባይ ስሜ የዕጣ ማውጣቱን ሥነ-ሥርዓት በይፋ አስጀምረዋል።

ግልጽነትን በተከተለ መንገድ በተካሄደው በዚህ የዕጣ አወጣጥ ሥነ-ሥርዓት መሠረትም የባንካችን የምስራቅ አዲስ ዲስትሪክት ሶስት ደንበኞች (የዕጣ ቁጥር900009435፣700002780 እና 800001365 )
ዕድለኛ የሆኑ ሲሆኑ፣ አራተኛው ዕድለኛ ደግሞ የምዕራብ አዲስ ደንበኛ (የዕጣ ቁጥር 400003858)ሆነዋል። ዕድለኛ ደንበኞች የፊፋ ዓለም ዋንጫ 2026™ ላይ በአካል በመገኘት ፈረንሳይ ከሴኔጋል ወይም እንግሊዝ ከጋና የሚያደርጉትን ጨዋታ ለመመልከት የሚያስችል ትኬቶችን የሚቀበሉ ይሆናል።

በሽያጭ ዘመቻው ላይ አስተያየታቸውን የሰጡት በቪዛ የምስራቅ አፍሪካ ክላስተር ኃላፊ አቶ ያሬድ እንዳለ “በቪዛ የዕለት ተዕለት ዲጂታል ክፍያዎች ለየት ላሉ ልምዶች በር መክፈት አለባቸው ብለን እናምናለን” ሲሉ ተናግረዋል።

አቶ ያሬድ ንግግራቸውን በመቀጠል “ይህ ከአቢሲንያ ባንክ ጋር እያካሄድን ያለነው የሽያጭ ዘመቻ ደህንነቱ የተጠበቀ እና ምቹ በሆነው የቪዛ ክፍያ ደንበኞች በዲጂታል መንገድ ለመክፈል መምረጣቸው እንደሚያሸልም እና እንደ ፊፋ የዓለም ዋንጫ 2026 ባሉ አለም አቀፍ መድረኮች ላይ ለመታደምም ዕድል እንደሚፈጠር ማሳያም ጭምር ነው። እንዲሁም በመላ ኢትዮጵያ የዲጂታል ክፍያን ለማስፋፋት እና የፋይናንስ አካታችነትን ለማፋጠን ያለንን የጋራ ቁርጠኝነት ያንፀባርቃል” ብለዋል።

በዚህ የሽያጭ ዘመቻ ጠንካራ የደንበኞች ተሳትፎ የታየ ሲሆን፣ ባለፈው ሳምንት ብቻ ወደ 7,000 የሚጠጉ ኩፖኖች የአቢሲንያ ባንክ ቪዛ ካርዶችን በመጠቀም ከ1,000 ብር በላይ ግብይቶችን ለፈጸሙ ደንበኞች ተሰራጭተዋል። ይህ ጠንካራ ምላሽ የደንበኞች ምቹ እና ደህንነቱን የጠበቀ የዲጂታል ክፍያ ዘዴዎችን የመቀበልና የመጠቀም ልምድ እያደገ መምጣቱን ያሳያል ።

የባንካችን የዲጂታል ከስተመር አኪዩዜሽን ዳይሬክተር አቶ አባይ ስሜ በበኩላቸው “ይህ የዕጣ አወጣጥ ሥነ-ሥርዓት ደንበኞቻችን የዲጂታል ክፍያዎችን እንዲጠቀሙ በማበረታታት እና በመሸለም ሂደት ወሳኝ ምዕራፍ ነው።ያየነው ጠንካራ ተሳትፎ በካርድ ላይ በተመሰረቱ ግብይቶች ላይ እያደገ የመጣውን ዕምነት እና በዕለት ተዕለት የባንክ ስራ ለደንበኞቻችን የተሻለ አገልግሎት ለማቅረብ ያለንን ቁርጠኝነት ያንፀባርቃል” ብለዋል።

አቶ አባይ ንግግራቸውን በመቀጠል “ከቪዛ ጋር ባለን አጋርነት የሃገራችንን የዲጂታል ክፍያ እርምጃ በማፋጠን አንዲሁም ደንበኞቻችን በፊፋ 2026 ዓለም ዋንጫን አይረሴ ጊዜ እንዲያሳልፉ ዕድል በመስጠታችን ኩራት ይሰማና!” ሲሉ ተናግረዋል።

ይህ የሽያጭ ዘመቻ በአቢሲንያ ባንክ እና በቪዛ መካከል በመላው ኢትዮጵያ የክፍያ ስርዓቶችን ፍጥነት፣ ደህንነት እና ቅልጥፍና ለማሻሻል ያለመ ሰፊ ስትራቴጂካዊ ትብብር አካል ነው። ትብብሩ የሚያተኩረው የዲጂታል ክፍያዎችን ተደራሽ ማድረግ፣ የፋይናንስ አካታችነትን መደገፍ፣ ፈጠራ እና ደንበኛ – ተኮር የሆኑ የክፍያ አማራጮችን ማቅረብ ላይ ነው።

በቀጣዮቹ ሳምንታት በሚኖሩ ቀጣይ ዙሮችም ተጨማሪ ዕጣዎች የሚወጡ ሲሆን፣ ይህም ደንበኞች ዕለት ተዕለት የቪዛ ካርድ ሲጠቀሙ የዓለም ዋንጫ ታዳሚ የመሆን ዕድል የሚሰጥ ይሆናል።

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Call Now Button