አቢሲንያ ባንክ፣ በኢትዮጵያ የፋይናንስ ዘርፍ በፍጥነት እያደገ ያለ የግል ባንክ ሲሆን፣ በኳታር 2022 የፊፋ የዓለም ዋንጫ™ ይፋዊ አጋር ከሆንው ከቪዛ ጋር በመተባበር እንደሚሰራ በታላቅ ደስታእያበሰረ ፤ አላማውም በኢትዮጵያ ገበያ የአቢሲንያ ቪዛ ካርድ ባለቤቶችን እና ተጠቃሚዎችን በካርድ መገበያየት በማበረታታት የዲጂታል ከፍያ አገልግሎቶችን ማሳደግ ነው።
የአቢሲኒያ ባንክና የቪዛ አጋርነት ዋና ሁነት የሚሆነው ሁለት እድለኛ የቪዛ ካርድ ተጠቃሚዎችና እነሱ የሚመርጧቸው ሁለት ተጫማሪ የቤተሰብ አባላት ወይም ጓደኞች ፣ በአጠቃላይ አራት ሰዎች ወደ ኳታር ለመጓዝ እስፖንሰር የሚደረጉበት ሲሆን የመጀመሪያዎቹ ሁለቱ ለመጀመሪያው ዙር ማጣሪያ ጨዋታዎች፣ ቀሪ ሁለቱ ደግሞ የሁለተኛው ዙር የምድብ ጨዋታዎችን ለመመልከት ከቪዛ የቀረበ ስጦታ ነው ። ይህ ታላቅ ሽልማት ባለ 5 ኮኮብ ሆቴል ውስጥ ለሁለት ምሽቶች ማረፊያ ፣የገበያ አበል ፣ከመድረክ ጀርባ በቅርበት ትእይንት የማየት ልምድ እና ሁለት ተከታታይ ጨዋታዎችን የማየት እድል ያካተተ ነው ። በዚሁ የፊፋ የዓለም ዋንጫ ኳታር 2022 ™ ዘመቻ ፤ባለ 55” ቴሌቪዥኖች፣ ላፕቶፖች፣ ስማርት ስልኮች፣ ፓወር ባንኮች እና ሌሎች አስደሳች ሽልማቶችም ለአቢሲንያ ቪዛ ካርድ ተጠቃሚዎች የቀረቡ ሲሆን በሽልማት እጣ ውስጥ የአቢሲንያ ቪዛ ካርድን በመጠቀም ብዙ ግብይት የፈጸሙ የካርድ ደንበኞች ይካተታሉ።
በዚህ ዘመቻ፤ የተለያዩ አዝናኝ እና አስደሳች እንቅስቃሴዎች የሚኖሩ ሲሆን ከአቢሲኒያ ጋር በካርድ ግብይት አብረው የሚሰሩ የንግድ ተቋማትና የባንኩ የተለያዩ ቅርንጫፎች የሚሳተፉባቸው ትእይንቶች፣ የመንገድ ላይ ትርኢቶች፣ የማህበራዊ ሚዲያ ተጽእኖ ፈጣሪዎችን በመጠቀም ከእግር ኳስ ጋር የተያያዙ የጎዳና ላይ መዝናኛዎች ላይ በማሳተፍ የሚሰጡ ሽልማቶች እንዲሁም በተመረጡ ቦታዎች ወይም የስፖርት ባሮች ውስጥ አስደሳች ጊዜያትን በመፍጠር የሚካሄዱ ይሆናሉ
የአቢሲንያ ባንክ እና የቪዛ ተወካዮች እንደገለጹት በዚህ አስደሳች የአጋርነት ዘመቻ የአቢሲንያ ቪዛ ካርድ ደንበኞች እና ተጠቃሚዎች ቪዛ ካርዳቸውን በተለያዩ የግብይት ማዕከላት በመጠቀም እንዲገበያዩ በማበረታታት ፤ ለሁሉም የእጣው ተሳታፊዎች መልካም ዕድል እንደሚመኙ ገልጽዋል ።
Leave a Reply