bankofabyssinia.com

Category: News

ባንካችን አቢሲንያ በሐምሌ ወር የውጭ ምንዛሬ ጥያቄ ላቀረቡ ደንበኞቹ 94 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር አቀረበ!
Post

ባንካችን አቢሲንያ በሐምሌ ወር የውጭ ምንዛሬ ጥያቄ ላቀረቡ ደንበኞቹ 94 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር አቀረበ!

አቢሲንያ ባንክ የውጭ ምንዛሪ እጥረትን ለመፍታት ብሎም በኢኮኖሚው የዋጋ መረጋጋት አንዲኖርና የደንበኞችን የገቢ ንግድ ለመደገፍ የበኩሉን አስተዋፆ እያደረገ የሚገኝ ሲሆን፣ በበጀት ዓመቱ በተለይም ለምግብ፣ እንዲሁም ለሌሎች ወደ ሀገራችን ለሚገቡ ስልታዊ ሸቀጦች (Strategic Commodities) ቅድሚያ በመስጠት ለደንበኞቹ በተለያየ መጠን የውጭ ምንዛሬ ሲያቀርብ ቆይቷል።በሐምሌ ወርም ባንካችን ከደንበኞቹ ለቀረቡት በርካታ የውጭ ምንዛሬ ጥያቄዎች አዎንታዊ ምላሽ በመስጠት ጥያቄዎቹን ያስተናገደ...

ማሳሰቢያ፤ ለተከበራችሁ ስማችሁ ከዚህ በታች ለተዘረዘረው የባንካችን ደንበኞች
Post

ማሳሰቢያ፤ ለተከበራችሁ ስማችሁ ከዚህ በታች ለተዘረዘረው የባንካችን ደንበኞች

ለተከበራችሁ ስማችሁ ከዚህ በታች ለተዘረዘረው የባንካችን ደንበኞች፣ ሂሳቦቻችሁ ለ15 ዓመትና ከዚያ በላይ ለሆነ ጊዜ ሳይንቀሳቀሱ በመቆየታቸው የእነዚህ ሂሳቦች ባለቤቶች ወይም ህጋዊ ባለመብቶች ነን የምትሉ ደንበኞች እስከ ጥቅምት 22 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ሂሳቦቹ በሚገኙባቸው ቅርንጫፎች ወይም በዋናው መ/ ቤት ህጋዊ ማስረጃችሁን በማቅረብ ክፍያዎቹን መጠየቅ ወይም ሂሳቦቹን ማንቀሳቀስ የምትችሉ መሆኑን በአክብሮት ለማሳወቅ እንወዳለን፡፡

ባንካችን አቢሲንያ በሁሉም ቅርንጫፎቹ ወረቀት አልባ የባንክ አገልግሎት መስጠት ጀመረ
Post

ባንካችን አቢሲንያ በሁሉም ቅርንጫፎቹ ወረቀት አልባ የባንክ አገልግሎት መስጠት ጀመረ

ባንካችን አቢሲንያ በዛሬው ዕለት በአዲስ መልክ በተዋቀረው የባንካችን ራስ ልዩ ቅርንጫፍ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዢ አቶ ማሞ ምህረቱ፣ የባንካችን ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ በቃሉ ዘለቀ፣ የበላይ የሥራ አመራሮችና ሠራተኞች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት የወረቀት አልባ የባንክ አገልግሎቱን በይፋ አስመርቆ ስራ አስጀምሯል።ይህ አዲስ አሠራር ገንዘብ ማስተላለፍ፣ ጥሬ ገንዘብ ማስገባትና ማውጣት፣ ሒሳብ መክፈትና ሌሎች በቅርንጫፍ በኩል...

ባንካችን አቢሲንያ የ2024/25 የበጀት ዓመት የሥራ አመራር ጉባዔውን አካሄደ
Post

ባንካችን አቢሲንያ የ2024/25 የበጀት ዓመት የሥራ አመራር ጉባዔውን አካሄደ

አቢሲንያ ባንክ የተጠናቀቀውን የ2024/25 በጀት ዓመት የሥራ አመራር ጉባዔውን ሐምሌ 17 እና 18 ቀን 2017 ዓ.ም በአፍሪካ ህብረት አዳራሽ ሲያካሂድ ቆይቶ ሊበረታቱና ሊሻሻሉ የሚገባቸውን የሥራ አፈፃፀሞች በመለየትና የባንኩን ቀጣይ ዓመት የትኩረት አቅጣጫዎች በማስቀመጥ በስኬት ተጠናቅቋል። በስብሰባው ላይ በዋና ዋና ቁልፍ መለኪያዎች አፈፃፀም ከዕቅድ አንፃር የተሠሩ ሥራዎች በዲስትሪክቶች በሰፊው የተነሱ ሲሆን አፈጻፀማቸው ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት አንፃር...

ሥነ ምግባራዊ አመራርነት ለተቋማዊ ተልዕኮ ስኬት
Post

ሥነ ምግባራዊ አመራርነት ለተቋማዊ ተልዕኮ ስኬት

ሥነ ምግባራዊ አመራርነት ለተቋማዊ ተልዕኮ ስኬት ለባንካችን ከፍተኛ አመራሮች ‘‘ሥነ ምግባራዊ አመራርነት ለተቋማዊ ተልዕኮ ስኬት’’ በሚል ርዕስ ጥር 30 እና የካቲት 1/ 2017 ዓ.ም በሀይሌ ግራንድ ሆቴል ስልጠና ተሰጠ፡፡ በስልጠናው የተገኙት የባንካችን ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ በቃሉ ዘለቀ ስልጠናውን አብረን በመውሰድ ወደ ተግባር መለወጥ ይገባል ብለዋል። ይህ ‹‹ሥነ-ምግባራዊ አመራርነት ለተቋማዊ ተልዕኮ ስኬት!›› በሚል ርዕስ ለሁለት...

ባንካችን አቢሲንያ የግማሽ አመት የስራ አፈፃፀም ግምገማ አካሄደ
Post

ባንካችን አቢሲንያ የግማሽ አመት የስራ አፈፃፀም ግምገማ አካሄደ

የአቢሲንያ ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ እና የስራ አመራር አባላት ባለፉት ስድስት ወራት በባንኩ በተሰሩ ዋና ዋና ክንውኖች ላይ ጥር 23 እና 24 ቀን 2017 ዓ.ም በሐይሌ ግራንድ ሆቴል በጋራ ግምገማ አካሂደዋል፡፡ በግምገማው ወቅት ከእቅድ አንፃር በዋና ዋና መለኪያዎች ረገድ የተሰሩ ስራዎች በዲስትሪክት ፅ/ቤቶች ተነስተው ሰፊ ውይይት የተደረገባቸው ሲሆን የባንካችን ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ በቃሉ ዘለቀ በአፈጻጸማቸው...

ባንካችን ዘመናዊ የባንክ አገልግሎት በካፌ የሚሰጠውን ማዕከል በድምቀት አስመረቀ
Post

ባንካችን ዘመናዊ የባንክ አገልግሎት በካፌ የሚሰጠውን ማዕከል በድምቀት አስመረቀ

ባንካችን አቢሲንያ በዋናው መስሪያ ቤት በሚገኘውና ከጫካ ቡና ጋር በመተባበር የከፈተውን ዘመናዊ የባንክ አገልግሎት በካፌ የሚሰጠውን ማዕከል በትላንትናው ዕለት ጥር 22 ቀን 2017 ዓ.ም የባንካችን ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ በቃሉ ዘለቀ፣ የጫካ ቡና ባለቤት አቶ ብስራት በላይ እንዲሁም ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በታላቅ ድምቀት አስመርቋል፡፡ አቢሲንያ ባንክ ሁሌም ቢሆን ዘመናዊ የሆኑ የባንክ አገልግሎቶችን በማቅረብ...

ለተከበሩ የአቢሲንያ ባንክ አ.ማ ባለአክሲዮን
Post

ለተከበሩ የአቢሲንያ ባንክ አ.ማ ባለአክሲዮን

የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለሥልጣን ጥቅምት 25 ቀን 2017 ዓ.ም በቁጥር ኢካገባ/ምዳ/019/17 በጻፈው ደብዳቤ በካፒታል ገበያ አዋጅ ቁጥር 1248/2013 መሰረት በሰነደ ሙዓለ ንዋይ አውጭዎች የተያዙ የሰነደ ሙዓለ ንዋይ ባለቤትነት መዝገቦች በማዕከላዊ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ግምጃ ቤት በሚዘጋጅ ባለቤትነት በኤሌክትሮኒክ ዘዴ በሚመዘገብበት የሂሳብ መዝገብ ስርዓት መተካት ያለበት በመሆኑ፤ ይህንን ለመፈጸም እንዲቻል የሰነደ ሙዓለ ንዋይ ባለቤቶችን (የባለአክሲዮኖችን) መረጃ...

ባንካችን አቢሲንያ 28ኛመደበኛ እና 15ኛው አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤውን አከናወነ!
Post

ባንካችን አቢሲንያ 28ኛመደበኛ እና 15ኛው አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤውን አከናወነ!

ሐሙስ፤ ኅዳር 05/2017 ዓ.ም  በአዲስ አበባ ከተማ በኢንተርሌክዥሪ ሆቴል በተካሄደው28ኛው መደበኛው እና 15ኛው አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ  መከናወኑን ተከትሎ ባንኩ በአጠቃላይ ሀብት፤ በተቀማጭ ገንዘብ፤ በአጠቃላይ ገቢ እንዲሁም በደምበኞች ቁጥር ዕድገት ማስመዝገቡን አስታውቋል፡፡ በዕለቱ  በተከናወነው የባለአክሲዮኖች ስብሰባ ላይ ባንካችን አቢሲንያ አጠቃላይ ሃብቱ 222.30 ቢሊየን ብር መድረሱ የተገለጸ ሲሆን ይህም ከባለፈው አመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የብር 32.79...

Call Now Button