ከዳያስፖራ ወገኖቻችን ምን ይጠበቃል?!

ከዳያስፖራ ወገኖቻችን ምን ይጠበቃል?!

የሰው ልጆች በምድር ላይ እስከኖሩ ድረስ የተጠናቀቀ ወይም ያለቀ አገር የላቸውም፡፡ አገር ሁል ጊዜ ሥራ የምትፈልግ በመሆኗ በትውልድ ቅብብሎሽ የምትደወር ጥጥ ናት፡፡ ምንም እንኳን በየዘመናቱ ልቃቂት ቢበዛባትም ጥጡን እየፈተለች ትጥላቸዋለች፡፡ ኢትዮጵያ ደግሞ ለዘመናት በልጆችዋ እጆች የተሠራች ያማረች ፈትል ናት፡፡

አገር ከልጆችዋ የምትጠብቃቸው እና የምትፈልጋቸው መሥዋዕቶች በየዘመናቱ ይኖራሉ፡፡ ኢትዮጵያ ዳር ድንበሯ ተጠብቆና ሉዓላዊነቷ ተከብሮ የኖረች በትላንቱ ትውልድ መሥዋትነት ነው፡፡ ቀደምት አባቶቻችን እና እናቶቻችን በአጥንታቸው እና ደማቸው አፅንተው አገር አስረክበውናል። ታዲያ በፀናው መሠረት ላይ የተረከብናት አገራችን፣ ለሚተካው ለማስቀጠል የዛሬው ትውልድ ድርሻ ብዙ ነው፡፡ እነኾ በአዲሷ ኢትዮጵያ የግንባታ ሒደት ላይ የድርችንን ጡብ ለማንበር ይኽን ቀላል ነገር ለአገራችን እናበርክት፡፡ ተከተሉን….

ሀገርን ለመውረር የመጣውን ጠላት ለመመለስ የሚፈለገው፣ ወደ ጦር ግንባር በመዝመት ሲኾን፤ የተጣባንን ድኅነት የምናሸንፈው ደግሞ ጠንካራ የኢኮኖሚ መሠረት መገንባት መሆኑን መዘንጋት የለብንም፡፡ አሁኑ በፀናው መሠረት ላይ ለመገንባት ኢትዮጵያ ልጆችዋን በተለያዩ ግንባሮች እያሰለፈች ነው፡፡ በውጪ የሚኖረው ሚልየኑ ዲዮስፖራ ለኢኮኖሚው ግንባር እንዲዘምት ጥሪ ቀርቦለታል፡፡ ግን ጥሪው የተሳካ ይኾን ዘንድ እና አገራችን ከገባችበት የኢኮኖሚ ቀውስ ለመውጣት እንዲህ ብናደርግስ…..

እንደሚታወቀው በርካታ ሀገራት በውጪ ሀገር ባሉ ዜጎቻቸው ዘርፈ ብዙ ችግሮቻቸውን ፈተዋል፡፡ ዜጎቻቸው በሕጋዊ መንገድ በሚልኩት Remittance የውጪ ምንዛሬ አያሌ ሳካዎችን አልፈዋል፤ በውጪ ያፈሩትን ሃብት በሀገራቸው ኢንቨስት በማድረግ የሥራ እድል ፈጥረዋል፤ የተማሩትን በሀገራቸው የዕውቀት ሽግግር በማድረግ የአሠራር እና የቴክኖሎጂ ለውጥ አምጥተዋል፡፡ ከእነዚህ አገራት መካከል ደቡብ ኮርያ፣ ሕንድ፣ ቻይና፣ ጃፓን እና ሜክሲኮ ይጠቀሳሉ፡፡

ከዛሬ 30 ዓመታት በፊት ጃፓናውያን እና ቻይናውያን ለትምህርት ወደ ተለያዩ አገራት በሚሄዱባቸው ጊዜ ከትምህርቱ ጎን ለጎን የፈጠራ ሥራዎችን በምስል የመሰብሰብ አገራዊ ግዴታ ተጥሎባቸው ነበር፡፡ በተለይ ደግሞ ሕንዳውያን እ.አ.አ ከ1999 ጀምሮ በሕጋዊ መንገድ በባንክ ሥርዐት ገንዘብ በመላክ ጠንካራ የሚኮኖሚ አቅም ሊፈጥሩ ችለዋል፡፡ በተያያዘ ወደ 35 ሚሊዮን የሚጠጉ የሕንድ ዲያስፖራ አባላት ወደ ሀገራቸው ገንዘብን ለመላክ ሕጋዊ መንገድን እንደሚጠቀሙ ይነገራል። እኛስ?!

በ85 አገሮች ወደ ሁለት ሚልዮን የሚጠጉ ኢትዮጵያውያን እንደሚኖሩ ይነገራል፡፡ እነዚህ በአማካይ ወደ አገር ቤት የሚልኩት ገንዘብ 78 በመቶ በጥቁር ገበያ የሚዘዋወር ነው፡፡ ይኽ ደግሞ በከፍተኛ ሁኔታ ኢኮኖሚውን በመጉዳት የውጪ ንግድ፣ በኢንቨስትመንት፣ በባንክ ኢንደስትሪ ላይ፣ ብድር የመክፈል ዐቅም ላይ ተፅእኖ ከመፍጠር አልፎ የኑሮ ውድነትን በማናርና የዋጋ ግሽበትን በመፍጠር የብር ዐቅም እንዲዳከም አድርጓል፡፡

በተለይም ዝውውሩ ከሕግና ከመዋቅር ውጪ በመሆኑ በባንክ የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችን በማዳከም የዓለም አቀፍ እና የሀገር ውስጥ የክፍያ ሥርዓቶች እንዲዛባ፣ ያልተረጋጋ የምንዛሬ ተመን እንዲኖር አስችሏል፡፡

በተቃራኒው በሕጋዊ መንገድ በባንክ ሥርዐት የሚከናወን ከሆነ ጥቅሙ ብዙ ነው፡፡ አንድም በአገር ላይ አንጻራዊ ሰላም የፈጠራል፤ የተረጋጋ ኢኮኖሚ ይፈጠራል፤ ዓለም አቀፍ አበዳሪዎች የሚሰጡትን ገንዘብ ከፍ በማድረግ ብድር የመክፈል አቅምን ይጨምራል፤ ዲሞክራሲያዊ እንዲሰፍን እና ጥቂቶች ብቻ ሀብት የሚያካብቱበትን ሒደት ያተካክለዋል፤ እንዲሁም የፋይናንስ ሥርዐቱን ያዘምናል፡፡

ባንካችን አቢሲንያ የተጣለበትን አገራዊ ኃላፊነት በመወጣት በተለያዩ መስኮች ሕዝብን በማገልገል ላይ ይገኛል፡፡ በመኾኑ በቅርቡ ለገና በዓል ወደ አገር ቤት እንዲመጡ ግብዣ የቀረበላቸው ዳያስፖራዎች፣ የተፈጠሩትን ችግሮች በማረጋጋት ረገድ እና በኢኮኖሚው ላይ የሚኖራቸው ጠቀሜታ እጅግ ከፍተኛ በመሆኑ በማመን ባዘጋጃቸው ልዩ ልዩ የባንኩ አገልግሎቶች እንዲጠቀሙ ይጋብዛል፡፡

እነኾ አቢሲንያ፣ ከምንጊዜውም በበለጠ ፈጣን እና ደህንነታቸው በተጠበቀ ከገንዘብ ማስተላለፊያ ተቋማት ጋር በጋራ እየሠራል ይገኛል። ለደንበኞቻችን Western Union, Money Gram, Dahabshiil, Xpress Money, Ria, Trans-Fast, World Remit, Thunes CashGo and Terrapay በመጠቀም ከየትኛውም የዓለም ክፍል ገንዘብ መላክ እና ለመቀበል የምትችሉ መኾኑ እናበሥራለን።

አቢሲንያ ከአገር ለአገር የቆመ የትጉኃን መናኸርያ!

በምኒልክ ብርሃኑ

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Call Now Button