ሰውን “ሰው” ለማድረግ

ሰውን “ሰው” ለማድረግ

ሰውን “ሰው” ያደረገው ምንድን ነው? ክብሩ ነው፣ ዕውቀቱ ነው፣ ሀብቱ ነው፣ ሕልሙ ነው?……. ጥያቄ አይደለም ….…. ግን ጥያቄ ቢሆንስ ……… መልሱ ሁሉም ናቸው ማለታችን አይቀርም፤ ምክንያቱም ሰው “ሰው” የሚሆንበት መንገድ ልዩ ልዩ በመሆኑ፣ ይህ ነው ብሎ መወሰን ስለማይቻል ነው፡፡

የተለያዩ ባህላዊ ልምዶች የበዙባት ኢትዮጵያ፣ እንደ ሕግ ተወስደው የሚተገበሩ በርካታ የኑሮ ዘይቤዎች አሏት፡፡ እነዚህ ዘይቤዎች ሕይወትን በማቅለል ዛሬ ላይ ማድረግ የምንፈልጋቸውን ነገሮች እንድናደርግ የሚ[h1] [h2] ግዙን መላዎች ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ አንዳንዴም እነዚህን ዘይቤዎች ተግባራዊ ማድረግ “ሰው” የመሆን መለኪያ ተደርጎ ሲቆጠር እናያለን፡፡ [h3] እንደዚህ ሊታመን የቻለበት ምክንያት ደግሞ ዘይቤዎቹን ተግባራዊ በማድረግ የሚታይ፣ የሚዳሰስ፣ የሚጨበጥ ለውጥ ማምጣት ስለተቻለ እና ስለሚቻል ነው፡፡

ከእነዚህ የኑሮ ዘይቤዎች መካከል በጉልህ የሚታየው፣ ዘይቤው ከመፈለጉ የተነሣ “ሰውን ሰው ያደረገው….” የሚል አባባል የተበጀለት፣ ከትንሽ እስከ ትልቁ፤ እንደ የአቅሙ ከደሃው እስከ ሀብታሙ፤ ከሎሌው እስከ ጌታው፤ ከምንደኛው (ደመወዝተኛ፣ ተቀጣሪ) እስከ ቀን ሠራተኛው፤ ከትልቅ ድርጅት ባለቤት እስከ ታክሲ ሹፌርና ረዳት፤ ከአለቃ እስከ ምንዝር ….. በሁሉም ማኅበረሰብ ውስጥ የሚተገበር ልምድ ነው ..…. ዕቁብ፡፡

ዕቁብ ማለት ሰዎች የገንዘብ እጥረት በሚያጋጥማቸው ጊዜ ለማሰባሰብ የሚጠቀሙበት ማኅበራዊ መረዳጃ ነው:: እንዳሁኑ ዘመን የባንክ እና የገንዘብ ሰጪ አገልግሎት ተቋማት ባልተስፋፋበት በቀደሙት ጊዜያት፤ በኢትዮጵያ ብድር የማግኘቱ አጋጣሚ ባብዛኛው የሌለ በመሆኑ ኅብረተሰቡ ዕቁብን በመጠቀም የተለያዩ ችግሮቹን የሚፈታበት እና ኑሮውን የሚያቀልበት መንገድ ነበር::

ዕቁብ ሦስት መሠረታዊ ነገሮች ያስፈልጉታል፤ አባላት፣ ጊዜ እና ገንዘብ፡፡፡ የአባላቱ መብዛት እና ማነስ በጊዜው ላይ እና በሚጣለው ገንዘብ ላይ ተጽዕኖ ያሳድራል፡፡ የአባላቱ ብዛት፣ ገንዘቡ የሚሰበሰብበት ርቀት (በቀን፣ በሳምንት ወይም በወር) እና የሚያልቅበት ጊዜ እንዲሁም የገንዘቡ መጠን የሚወሰነው ገንዘቡን ለማሰባሰብ በጀመረው ሰው ወይም በዕቁብ መሥራቹ(ቾቹ) ነው፡፡

ማንኛውም ዕቁብ በአብዛኛው ጊዜ የሚጀመረው በሰብሳቢው ነው፡፡ ሰብሳቢው ገንዘቡን ፈልጎ ዕቁቡን ስለሚያስጀምር በመጀመሪያ ዙር የተሰበሰበውን ገንዘብ የሚወስድ እርሱ ነው፤ የሚቀጥሉት ደግሞ  በዕጣ ለሚለዩት ተረኞች ይደለደላሉ::

የዕቁብ ትልቁ ፋይዳ ለረጅም ጊዜ ቆጥበን የማናገኘውን ገንዘብ በአንድ ጊዜ እንድናገኝ በማድረግ፣ የምንፈልገውን ነገር በቶሎ እንድናደርግ እድሉን ማስቻሉ ነው፡፡ ዕቁብ በተለምዶ የሚከናወነው በመተዋወቅ እና በመተማመን ሲሆን ትላልቅ ገንዘብ የሚሰበሰብበት ከሆነ ደግሞ፤ ሕጋዊ በሆነ መልኩ ሰብሳቢ፣ ጸሐፊ እና ጠበቃ ሳይቀር በመቅጠር በክፍያ የሚያስተዳድሩት አባላት ይኖሩታል:: በእንደዚህ ዐይነት ሁኔታ ደግሞ ባለዕጣው በደረሰው ጊዜ ተያዥ የማምጣት የግድ ይኖርበታል ማለት ነው::

በዚህ መሠረት እንደ ዕቁቡ መጠን በሚሰበሰበው ገንዘብ ሀብት እና ንብረት ያፈሩ፤ ድርጅቶችን እና ተቋማትን የከፈቱ፤ ንግዳቸውን፣ ትምህርታቸውን፣ ዐቅማቸውን ያሻሻሉ፤ የሚፈልጉትን ነገር ማድረግ የቻሉ በርካቶች ናቸው፡፡ እንዲህ የማድግ ዐቅም ዕቁብ ካለው ……. አሁን አሁን ከላይ ክፍት ያደረግነውን አባባል እንሙላ፤ “ሰውን ሰው ያደረገው ዕቁብ ነው”፡፡ ይህ ብሒል፣ የጉዳዩን ወይም የዕቁብን ክብደት ብቻ ሳይሆን፤ ዕቁብ በሰዎች ሕይወት ላይ የሚያሳድረውን አዎንታዊ ተጽዕኖ የሚነግረን በመሆኑ ነው፡፡ እንዴት….

ዕቁብ ከገንዘብ ባለፈ ማኅበራዊ ግንኙነት በመፍጠር እና በማጠናከር፤ እርስ በእርስ በማቀራረብ እና በማስተዋወቅ፤ ኑሮን በማዘመን ረገድ ፋይዳው የጎላ ነው፡፡ አሁን አሁን ደግሞ ዘመኑ በደረሰበት ቴክኖሎጂ በመታገዝ በግለሰብ ብቻ ሳይሆን ሕጋዊ ሰውነት ባለው ተቋም ደረጃ በማሳደግ ዲጂታላይዝ ዕቁብ ሰብሳቢዎች ብቅ እያሉ ነው፡፡

ባንካችን አቢሲንያ ማንኛውም ከዕቁብ ሰብሳቢ ግለሰቦችም ሆኑ ተቋማትም ጋር አብሮ ለመሥራት አሠራሩን እያዘመነ ሲሆን የዚህ እድል ተጠቃሚ ትሆኑ ዘንድ በሩን ክፍት አድርጎ ይጠብቃችኋል፡፡

አቢሲንያ የሁሉም ምርጫ!

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Call Now Button