ኢትስዊች አክሲዮን ማህበር ጥቅምት 18 ቀን 2018 ዓ.ም በሸራተን አዲስ ባካሄደው 12ኛው ዓመታዊ የባለአክሲዮኖች ስብሰባ ማጠናቀቂያ ላይ ባንካችን አቢሲንያ እ.ኤ.አ በ2024/25 በጀት ዓመት በባንክ ለባንክ ግብይት ላስመዘገበው የላቀ አፈጻጸም የዕውቅና ሽልማት አበርክቶለታል።
በዚህም መሰረት ባንካችን አቢሲንያ እ.ኤ.አ በ2024/25 በጀት ዓመት በአጠቃላይ የባንክ ለባንክ የኤ.ቲ.ኤም ግብይት አፈጻጸም ከሁሉም የግል ባንኮች ጋር ተወዳድሮ የአንደኝት ደረጃን አግኝቷል። በተጨማሪም በበጀት ዓመቱ በአጠቃላይ የባንክ ለባንክ የፖስ ግብይት የሁለተኛነት ደረጃን ለመያዝ ችሏል።
በዕለቱ የዲጂታል ባንኪንግ ኦፕሬሽንስ ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ዳንኤል ረታ ባንካችን አቢሲንያን በመወከል የዕውቅና ሽልማቱን ተቀብለዋል።
ኢትስዊች አክሲዮን ማህበር እ.ኤ.አ በ2024/25 በጀት ዓመት የብር 741.1 ቢሊዮን ዋጋ ያላቸው 287.4 ሚሊዮን የባንክ ለባንክ ግብይቶችን እንዳካሄደ በዕለቱ ተገልጿል።


 
 

Leave a Reply