bankofabyssinia.com

ባንካችን አቢሲንያ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ባዘጋጀው ዓመታዊ “የፋይናንስ ዕውቀት ሳምንት” ላይ እየተሳተፈ ይገኛል

ባንካችን አቢሲንያ ትናንት ጥቅምት 17 ቀን 2018 ዓ.ም በጋምቤላ ከተማ በድምቀት በተጀመረው የፋይናንስ ዕውቀት ሳምንት (Financial Literacy Week) የመክፈቻ መርሃ-ግብር ላይ እየተሳተፈ ይገኛል፡፡

“የፋይናንስ ትምህርትን ማጎልበትና የደንበኞች ጥበቃን ማጠናከር” በሚል መሪ ቃል በሃገር-አቀፍ ደረጃ እየተካሔደ በሚገኘው በዚህ የመክፈቻ ፕሮግራም ላይ የጋምቤላ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ-መስተዳድር ወ/ሮ አለሚቱ ኡሞድን ጨምሮ፣ የክልሉ መንግስት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ የተለያዩ የፋይናንስ ተቋማት ተወካዮችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እየተሳተፉ ይገኛል፡፡

የባንካችን ተወካዮችም ባንካችን አቢሲንያ በደንበኞች ጥበቃ ዙሪያ በርካታ ስራዎችን እየሰራ እንደሆነና ከእነዚህም መካከል የደንበኞች የጣት አሻራና የፊት-ገጽታ መረጃ ምዝገባ ዋነኛው እንደሆና ገልጸዋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ባንካችን በቅርቡ የጀመረውን የወረቀት አልባ የባንክ አገልግሎትና ለህብረተሰባችን ይበልጥ ተደራሽ ለመሆን በየጊዜው የሚያወጣቸውን ፕሮዳክቶች በዋናነትም አፖሎን በተመለከተ ገለጻ አድርገዋል፡፡

መርሃ-ግብሩ ሃገር አቀፉን የፋይናንስ ትምህርት ስትራቴጂ መሰረት በማድረግ የሴቶችንና ተጋላጭ የሆኑ ህብረተሰብ ክፍሎችን የሞባይል ፋይናንስ እና የዲጂታል ባንኪንግ ዕውቀት ከፍ ማድረግን አላማው ያደረገ እንደሆነ በመድረኩ ተገልጿል። በዚህም ወደ 3 ሚሊዮን የሚሆኑ ወጣቶች ከነሱም ውስጥ ግማሽ የሚሆኑ ሴቶችን የትኩረት ማዕከል አድርጓል። 

ከትናንት ጥቅምት 17 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ መጪው አርብ ጥቅምት 21 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ በሚቆየው በዚህ መርሃ-ግብር የማህበረሰብ አቀፍ ወርክሾፕ፣ የመድረክ ውይይቶች፣ የመስክ ጉብኝቶች፣የተለያዩ ስልጠናዎች እና አውደ ጥናቶች ተካትተዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Call Now Button