bankofabyssinia.com

ባንካችን ባለ 2 መኝታ የመኖሪያ አፓርታማ ለዕድለኛው አስረከበ

ባንካችን ባለ 2 መኝታ የመኖሪያ አፓርታማ ለዕድለኛው አስረከበ

ባንካችን አቢሲንያ የዲጂታል ግብይቶችን ለማበረታታት እና አዳዲስ የዲጂታል ባንክ ደንበኞችን ለማፍራት ባዘጋጀው መርሐ-ግብር (Merchant Engagement Campaign) ዕጣ ለወጣላቸው የባንካችን ደንበኛ ሽልማታቸውን አስረከበ።

ዛሬ የካቲት 5 ቀን 2018 ዓ.ም በሃይሌ ግራንድ ሆቴል በተካሄደ ዝግጅት ላይ የባንካችን ቺፍ ዲጂታል ባንኪንግ ኦፊሰር ወ/ሮ ሶስና መንገሻ ለዕድለኛው የአባመላ ቅርንጫፍ ደንበኛ ለአቶ መሐመድ ከድር በአርሞንኤም ሪል ስቴት የተገነባና ሃያት አካባቢ የሚገኝ ባለ 2 መኝታ የመኖሪያ አፓርታማ አስረክበዋል።

ወ/ሮ ሶስና ሽልማቱን ለዕድለኛው ካስረከቡ በኋላ “ይህ መርሐ-ግብር በዋናነት ህብረተሰባችን የዲጂታል ግብይትን ባህሉ እንዲያደርግ የሚያበረታታ ሲሆን ዛሬ ላይ ደግሞ ባንካችን ደንበኞች ባሉበት ሆነው ሁሉንም የባንክ አገልግሎቶች የሚያገኙበትን ዘመናዊ የባንክ ቴክኖሎጂ ለዘመኑ የዲጂታል ትውልድ አቅርቧል” ብለዋል።

የአዲስ አበባ ነዋሪ የሆኑትና በንግድ ሥራ የሚተዳደሩት አቶ መሐመድም ሽልማቱን ከተረከቡ በኋላ ስሜታቸውን ሲገልጹ “የምኖረው በኪራይ ቤት ስለሆነ፣ ከባንኩ ተደውሎ ቤት ደርሶሃል ስባል መጀመሪያ ለማመን ተቸግሬ ነበር” በማለት ተናግረዋል። 

ይህ መርሐ-ግብር ይፋ ከተደረገበት ከሚያዚያ 28 ቀን 2017 ዓ.ም እስከ መስከረም 27 ቀን 2018 ዓ.ም ጊዜ ውስጥ ከ10 ሚሊዮን በላይ ግብይቶች የተከናወኑ ሲሆን፣ በዚህም ከብር 138 ቢሊዮን በላይ ማንቀሳቀስ ተችሏል።

በሽልማት ርክክብ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የባንካችን የበላይ ሥራ አመራር አባላት፤ የመምሪያ እና የዲስትሪክት ዳይሬክተሮች፣ የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት ተወካዮች እንዲሁም ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Call Now Button