የአቢሲንያ ቤተሰብ ቀን በድምቀት ተከበረ!

የአቢሲንያ ቤተሰብ ቀን በድምቀት ተከበረ!

የአቢሲንያ ቤተሰብ ቀን የካቲት 1 ቀን 2018 ዓ.ም የባንካችን ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ በቃሉ ዘለቀን ጨምሮ ሌሎች የባንካችን አመራሮችና መላው የባንካችን ሠራተኞች በተገኙበት በወዳጅነት ፓርክ በድምቀት ተከበረ።

ዝግጅቱን በንግግር የከፈቱት የባንካች የኮርፖሬት ሂውማን ሪሶርስ ቺፍ ኦፊሰር አቶ ሰይፉ ቦጋለ እንደተናገሩት “የአቢሲንያ ቤተሰብ ቀን” የሚለው ጠንካራ መሪ ቃል ሁላችንም በአንድ ራዕይ በጋራ ለአንድ አላማ የምንተጋ የአቢሲንያ ቤተሰብ መሆናችንን በጉልህ የሚያንጸባርቅ ነው ብለዋል፡፡ 

ይህ ቀን ምስጋና እና እውቅና የመስጠት ቀንም ጭምር ነው ሲሉ ያከሉት አቶ ሰይፉ፣ የባንኩን ሠራተኞች በሙሉ ባለፉት አመታት ላሳዩት የሥራ ትጋት፣ ፕሮፌሽናሊዝም እና ጥንካሬ ምስጋና አቅርበዋል።

በዕለቱ በባንኩ ረጅም ዓመታት ላገለገሉ ሠራተኞች ዕውቅና የተሰጠ ሲሆን ከባንኩ ምስረታ ጀምሮ ላለፉት 30 ዓመታት ላገለገሉ ሠራተኞች የባንኩ ዓርማ ያለበት የወርቅ ሃብል፣ እንዲሁም 25 ዓመትና ከዚያ በላይ ላገለገሉ ሠራተኞች ደግሞ የዕውቅናና የምስጋና ዋንጫ (ክሪስታል) ተበርክቷል። 

በተጨማሪም የፎቶግራፍ ዓውደ ርዕይ፣ ሠራተኞችን ዕድለኛ የሚያደርግ ዕጣ፣ በ2000 ሃበሻ ባንድ የቀረበ ሙዚቃና በኮሜዲያን አዝመራው የቀረበ ዝግጅት የቤተሰብ ቀኑ አካል ነበሩ።

የአቢሲንያ ቤተሰብ ቀን በተመሳሳይ ከአዲስ አበባ ውጭ በሚገኙ በሁሉም የባንካችን ዲስትሪክቶች ጭምር በርካታ ሠራተኞች በተገኙበት በድምቀት ተከብሯል።

በዚህ ዝግጅት ላይ የባንካችን የቀድሞ አመራሮች፣ የመቄዶንያ በጎ አድራጎት ማህበር መስራች ቢንያም በለጠ (የክብር ዶ/ር)፣ ታዋቂው የኪነጥበብ ባለሙያ ጌትነት እንየው፣ የሚዲያ ባለሙያዎች እንዲሁም ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Call Now Button