ለአቢሲንያ ባንክ አ.ማ. ባለአክሲዮኖች የተደረገ የመደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ የስብሰባ ጥሪ

ለአቢሲንያ ባንክ አ.ማ. ባለአክሲዮኖች የተደረገ የመደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ የስብሰባ ጥሪ

የአቢሲንያ ባንክ አ.ማ. 25ኛ ዓመታዊ መደበኛ የባለአክሲዮኖች ጠቅላላ ጉባዔ ሐሙስ ታህሳስ 7 ቀን 2014 ዓ.ም. ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት ጀምሮ አዲስ አበባ ካዛንቺስ አካባቢ በሚገኘው ኢንተር ሌግዠሪ ሆቴል (በቀድሞ ስሙ ኢንተርኮንቲኔታል አዲስ ሆቴል) የሚካሄድ በመሆኑ ባለአክሲዮኖች ከላይ በተጠቀሰው ቦታና ቀን ተገኝታችሁ በጉባዔው እንድትሳተፉ የዲሬክተሮች ቦርድ በአክብሮት ጥሪውን ያቀርባል፡፡

  1. የ25ኛው ዓመታዊ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ አጀንዳዎች
    1.1. የጉባዔውን አጀንዳ ማጽደቅ፣
    1.2. አዳዲስ ባለአክሲዮኖችን መቀበልና የተደረጉ የአክሲዮን ዝውውሮችን ማሳወቅ፣
    1.3. የዳይሬክተሮች ቦርድን እ.ኤ.አ. የ2020/2021 ዓመታዊ ሪፖርት ማዳመጥ፣
    1.4. የውጪ ኦዲተሮችን እ.ኤ.አ. የ2020/2021 የሒሳብ ዘመን ሪፖርት ማዳመጥ፣
    1.5. በተራ ቁጥር 1.3 እና 1.4 ሥር በቀረቡት ሪፖርቶች ላይ ተወያይቶ ማጽደቅ፣
    1.6. እ.ኤ.አ. በ2020/2021 የሒሣብ ዘመን የተጣራ ትርፍ አመዳደብና አከፋፈል ላይ ውሳኔ ማሳለፍ፣
    1.7. እ.ኤ.አ. የ2021/2022 የሒሳብ ዘመን የውጪ ኦዲተሮችን መሾምና የአገልግሎት ክፍያቸውን መወሰን፣
    1.8. እ.ኤ.አ. የ2020/2021 በጀት ዓመት የዳይሬክተሮች ቦርድ ዓመታዊ የሥራ ዋጋ መወሰን፣
    1.9. እ.ኤ.አ. የ2021/22 በጀት ዓመት የዳይሬክተሮች ቦርድ ወርሃዊ አበል ክፍያ መወሰን፣
  2. ማሳሰቢያ
    2.1. በጉባዔው ላይ የሚገኙ ባለአክሲዮኖች ኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመከላከል የኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ባወጣው መመሪያ መሠረት የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል (ማስክ) ማድረግ እና ሌሎች የጥንቃቄ እርምጃዎችን መከተል ይጠበቅባቸዋል፡፡
    2.2 ባለአክሲዮኖች በጉባዔው ላይ ለመሳተፍ የመጠቀሚያ ጊዜው ያላለፈበት መታወቂያ ወይም ፓስፖርት ይዘው መቅረብ አለባቸው፡፡
    2.3. በጉባዔው ላይ በግንባር ለመገኘት የማይችሉ ከሆነ በወኪልዎ አማካኝነት መሳተፍ ይችላሉ፡፡ ለዚህም፣
    2.3.1. ጉባዔው ከሚካሄድበት ከሦስት የሥራ ቀናት በፊት ለገሃር በሚገኘው በባንኩ ዋና መሥሪያ ቤት 2ኛ ፎቅ የፋይናንስ እና ሂሣብ መምሪያ ቢሮ ቁጥር 219 ቀርበው ለዚሁ ዓላማ ባንኩ ያዘጋጀውን የውክልና መስጫ ቅጽ በመፈረም፣ ወይም
    2.3.2. ውል ለማዋዋል ሥልጣን በተሰጠው አካል የተረጋገጠና በጉባዔው ለመካፈል የሚያስችል የውክልና ሥልጣን የተሰጣቸው ወኪልዎ በዕለቱ በጉባዔው ቦታ የውክልና ሠነዱን ኦሪጅናልና አንድ ፎቶ ኮፒ ይዘው በመቅረብ በጉባዔው መሳተፍ ይችላሉ፡፡
    የአቢሲንያ ባንክ አ.ማ. የዳይሬክተሮች ቦርድ

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Call Now Button