bankofabyssinia.com

የባንካችን “ከአቢሲንያ ባንክ ጋር ይጀምሩ – ያድሱ እና ይደጉ” የሽልማት መርሃ-ግብር የመጀመሪያ ዙር ዕድለኞች ይፋ ሆኑ

የባንካችን “ከአቢሲንያ ባንክ ጋር ይጀምሩ – ያድሱ እና ይደጉ” የሽልማት መርሃ-ግብር የመጀመሪያ ዙር ዕድለኞች ይፋ ሆኑ

ከኅዳር 22 – ጥር 21, 2018 ዓ.ም ድረስ እየተካሄደ በሚገኘውና “ከአቢሲንያ ባንክ ጋር ይጀምሩ – ያድሱ እና ይደጉ” በተሰኘው የሽልማት መርሃ-ግብር የመጀመሪያ ዙር ተሸላሚዎች ይፋ ሆነዋል።

ትናንት ታህሳስ 7 ቀን 2018 ዓ.ም በዋናው መ/ቤት አዳራሽ ዴፒዩቲ ቺፍ ከስተመር ሪሌሽንሺፕና አክዊዜሽን ኦፊሰር የሆኑት አቶ ወሰንየለህ አበራና ሌሎች  የባንካችን የስራ ሃላፊዎች እንዲሁም የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት ታዛቢዎች በተገኙበት ላይ ሁለት ስማርት ስልኮችን እና ሁለት ፍሪጆችን የሚያስገኙት የዕጣ ቁጥሮች ወጥተዋል።

በዚህም መሠረት ሁለት ስልኮች የሚያስገኙት የዕጣ ቁጥሮች በሁለቱም ሃዋሳ ዲስትሪክት የወጡ ሲሆን እነሱም 0778300036515 እና 0405200284262 ሆነዋል። ሁለት ፍሪጆችን የሚያስገኙት የዕጣ ቁጥሮች ደግሞ የማዕከላዊ አዲስ ዲስትሪክትና የምስራቅ አዲስ ዲስትሪክት  ደንበኞችን ዕድለኛ ያደረጉ ሲሆን አነሱም0189900514365 እና 0106600382433 ወጥተዋል።

ለሁለት ወራት የሚቆየው ይህ የሽልማት መርሃ-ግብር በዋናነትዘመናዊ ሃዩንዳይ ኤሰንት ሴዳን መኪና ዕጣን የያዘ በየ15 ቀኑ የሚወጡ በርካታ ላፕቶፖች፣ ቴሌቪዥኖች፣የልብስ ማጠቢያ ማሽኖችና ሌሎች ስጦታዎችንም አካትቷል።

ባንካችን ዕድለኞችን ”እንኳን ደስ አላችሁ ! ” እያለ ሌሎች ደንበኞችም በፊት ገፅታ እና በጣት አሻራ የደንበኝነት ምዝገባ በማካሄድ፣  በቅርንጫፍም ሆነ በዲጂታል አማራጮች አዲስ ሂሳብ በመክፈትና ተቀማጭ በማድረግ ፣ ነባር ሂሳብ ላይ ተጨማሪ ገቢ በማድረግ እና ሌሎች አገልግሎቶችን በመጠቀም ይሸለሙ!

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Call Now Button