ባንካችን አቢሲንያ በአዲሱ የኢትዮ-ቴሌኮም ቴሌብር የሞባይል ገንዘብ አገልግሎት በአጋርነት መሥራት ጀመረ

ባንካችን አቢሲንያ በአዲሱ የኢትዮ-ቴሌኮም ቴሌብር የሞባይል ገንዘብ አገልግሎት በአጋርነት መሥራት ጀመረ

ኢትዮ-ቴሌኮም እና አቢሲንያ ባንክ ባደረጉት ስምምነት አዲሱ የኢትዮ-ቴኮም ቴሌ ብር አገልግሎት በሁሉም የባንካችን ቅርንጫፎች የባንካችን ደንበኞች ለሆኑ እና ላልሆኑ ሁሉ ወደ ቴሌ ብር አካውንት ገንዘብ ገቢ የማድረግ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል፡፡

አገልግሎቱም፡-

1- የባንካችን ደንበኞች ቢሆኑም ባይሆኑም ማንኛውም ግለሠብ በባንካችን ቅርንጫፍ መስኮቶች በመጠቀም ቀደም ብሎ ወደ ከፈተው የቴሌብር አካውንት በጥሬ ገንዘብ ወይም ከአካውንት ወደ ቴሌብር ሂሳባቸው ገቢ ማድረግ ይችላል፡፡

2- የባንካችን ደንበኛ ሆኖ የባንካችን የኢንተርኔት/ሞባይል ባንክ ተጠቃሚ ከሆኑ ደንበኞች በቀላሉ ከሂሳባቸው ወደ ቴሌብር ገንዘብ ማዘዋወር ይችላል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Call Now Button