ባንካችን አቢሲንያ የሽልማት መርሀ ግብር አካሄደ

ባንካችን አቢሲንያ የሽልማት መርሀ ግብር አካሄደ

ባንካችን አቢሲንያ “መቆጠብ ያሸልማል” በሚል የአገር ውስጥ ቁጠባን የሚያበረታታ መርሀ ግብርን ለ4ኛ ግዜ፣ “እንሸልምዎ” በሚል መሪ ቃል የውጭ ምንዛሬ የሚያበረታታ መርሀ ግብርን ለ5ኛ ግዜ፣ ከታህሳስ 25 ቀን 2015 ዓ.ም እስከ ሰኔ 24 ቀን 2015 ዓ.ም አከናውኖ ባሳለፍነው ነሐሴ 04 ቀን 2015 ዓ.ም. በብሄራዊ ሎተሪ አዳራሽ የዕጣ አወጣጥ ስነ-ስርዓት አከናውኖ ባለዕድለኞችን መለየቱ የሚታወስ ነው ፡፡

በዚህም መሰረት ዘመናዊ አይሱዙ ኤን.ፒ.አር ፣ዘመናዊ ትራክተር፣የ 5 ቀናት የቱርክ ሀገር ጉብኝትን ጨምሮ በሁለቱም ዝግጅቶች 187 ሽልማቶችን ያካተተው መርሀ ግብራችን በመላው ሀገሪቱ የሚገኙ ከ 8 ሚሊየን በላይ ደንበኞች በዕጣው የተሳተፉበትም ነበር ፡፡

እነዚህ ዕድለኞች በድሬደዋ፣ በደሴ፣ በሀዋሳ ፣በአዲስ አበባ እና በመላው ሀገሪቱ የሚገኙ ሲሆኑ ባንካችን አቢሲንያ በቃሉ መሰረት ለዕድለኞች በያሉበት ከተማ በደማቅ ስነ-ስርዓት አስረክቧል፡፡
በዚህ የእጣ መርሀግብራችን ለተሳተፉ በሙሉ ልባዊ ምስጋናችንን እናቀርባለን፡፡ ለባለ ዕድለኞች እንኳን ደስ አላችሁ እያልን መሰል የሽልማት መርሀ ግብር በቅርቡ በአይነት እና በይዘት ላቅ ብሎ ለመምጣት ዝግጅት ማጠናቀቃችንን እያበሰርን በመላው ሀገሪቱ የሚገኙ የባንካችን ደንበኞች በነዚሁ ዝግጅቶቻችን ላይ በመሳተፍ የባንካችን አገልግሎት ተጠቃሚ እንዲሆኑ፣ እድላቸውንም እንዲሞክሩ እንጋብዛለን ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Call Now Button