ባንካችን ከአዋጭ የገንዘብ ቁጠባና ብድር መሠረታዊ የህብረት ሥራ ማህበር ጋር የኮር ባንኪንግ ሥራዎችን የሚያስተሳስር የሲስተም ልማት (System Integration) የትግበራ ውል ስምምነት ሰነድ ተፈራረመ፡፡

ባንካችን ከአዋጭ የገንዘብ ቁጠባና ብድር መሠረታዊ የህብረት ሥራ ማህበር ጋር የኮር ባንኪንግ ሥራዎችን የሚያስተሳስር የሲስተም ልማት (System Integration) የትግበራ ውል ስምምነት ሰነድ ተፈራረመ፡፡

የሲስተም ልማት(System Integration) ትግበራው፣ የማህበሩ አባላት ወርሀዊ ቁጠባቸውንም ሆነ የብድር ክፍያቸውን በባንኩ በሚገኘው የህብረት ሥራ ማህበሩ ሂሳብ ላይ ሲያስገቡ በዚያው ፍጥነት (Real Time) አዋጭ በሚገኘው ሂሳባቸው ላይ ማስተላለፍ እንዲሁም የባንኩንና የህብረት ሥራ ማህበሩን ሂሳብ የማወራረድ ሥራን የሰው ጣልቃ ገብነት በሌለው መንገድ ማከናወን የሚያስችል ሲሆን፣ ይህም ለሌሎች የዲጂታልና ኤሌክትሮኒክ ማበልፀግ ሥራ በር ከፋችና አመቺነትን የፈጠረ መሆኑም ተገልጿል፡፡የመግባቢያ ስምምነቱን የአዋጭ የኮር ባንኪንግ እና ሶፍትዌር ማስፋፊያ ሀላፊ በሆኑት አቶ ሰለሞን ወሌ እና የአቢሲንያ ባንክ ምክትል ዋና ሪቴል ኦፕሬሽን የሆኑት አቶ ኤልያስ ካሳ ፈርመዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Call Now Button