ባንካችን የአፍሪካ ዋንጫ መክፈቻ ሰነ ስርዓትን እንዲሁም ሀገራችን ያደረገችውን የመክፈቻ ጨዋታ መርሐ-ግብር በጊዮን ግሩቭ ጋርደን በደማቅ ሁኔታ አካሄደ!

ባንካችን የአፍሪካ ዋንጫ መክፈቻ ሰነ ስርዓትን እንዲሁም ሀገራችን ያደረገችውን የመክፈቻ ጨዋታ መርሐ-ግብር በጊዮን ግሩቭ ጋርደን በደማቅ ሁኔታ አካሄደ!

አቢሲንያ ባንክ ከቪዛ ካርድ ጋር በመተባበር የቶታል ኢነርጂስ አፍሪካ ዋንጫ መክፈቻ ስነ ስርዓትን እንዲሁም ሀገራችን ኢትዮጵያ ከኬፕ ቨርድ ጋር እሁድ ጥር 1 ቀን ያደረጉትን የጨዋታ ፕሮግራም በጊዮን ግሩቭ ጋርደን በደማቅ ሁኔታ አካሄደ፡፡በዝግጅቱ ላይ በርካታ ጥሪ የተደረገላው እንግዶችና ተመልካቾች የተገኙ ሲሆን፣ የባንካችን የበላይ አመራሮችም ኬክ በመቁረስ እንዲሁም ለዋሊያዎቹ የመልካም ምኞት መልዕክት በማስተላለፍ ዝግጅቱን አሰጀምረዋል፡፡ተጋባዥ ሙዚቀኞችም ከሐሴት ባንድ ጋር በመሆን የተለያዩ ጣዕም ያላቸውን ዜማዎች ለተመልካቾች በማቅረብ የዝግጅቱን ታዳሚዎች በማዝናናት አሳልፈዋል፡፡ይህ መርሐ-ግብር ሀገራችን ኢትዮጵያ ከካሜሩን ጋር ሀሙስ ጥር 5 ቀን የምታደርገውን ጨዋታ ጨምሮ በቀጣይም ሀገራችን ጨዋታ በሚኖራት ቀናት ሁሉ የሚዘጋጅ ነው፡፡ በወቅቱ በመስቀል አደባባይ ዙሪያ በነበረው ተደራራቢ ፕሮግራሞች ምክንያት የነበረው መጨናነቅ ሳያስቸግራቸው፣ በርካታ የዋልያዎቹ ደጋፊዎች በመርሐ-ግብሩ ለመታደም ችለዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Call Now Button