ባንካችን የክርስትና እምነት ተከታዮችን ታሳቢ በማድረግ ያዘጋጀውን የአሥራት በኩራት አገልግሎት አስተዋወቀ

ባንካችን የክርስትና እምነት ተከታዮችን ታሳቢ በማድረግ ያዘጋጀውን የአሥራት በኩራት አገልግሎት  አስተዋወቀ

አቢሲንያ ባንክ የክርስትና እምነት ተከታዮችን ታሳቢ በማድረግ ያዘጋጀውን ‹‹የአሥራት በኩራት›› አገልግሎት ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ፓትሪያርክ ለብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ አስተዋወቀ!!! ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት በዛሬው ዕለት የአቢሲኒያ ባንክ ከፍተኛ አመራሮችን በጽ/ቤታቸውተቀብለው አነጋግረዋል። የባንኩ የሥራ ሓላፊዎች ከቅዱስነታቸው ጋር በነበራቸው ቆይታ ባንኩ በዚህ ዓመት መላው ክርስቲያን ምእመናንን ታሳቢ በማድረግ ያዘጋጀውን የአሥራት በኩራት ማስቀመጫ መርሐ ግብር አስተዋውቀው ከቤተ ክርስቲያኒቱ ጋር ለመሥራት ያላቸውን ፍላጎት አስረድተዋል።ቅዱስነታቸውም ባደረጉት የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር በቀድሞው የኢትዮጵያ ስያሜ የሚጠራው አቢሲኒያ ባንክ የያዘው ትልቅ ስም እንደመሆኑ መጠን እየሠራ ያለውም ትልቅ ሥራ መሆኑን አድንቀው ከአሥራት በኩራት ጋር ተያይዞ የቀረበውን ሐሳብ በተመለከተ የሚመለከታቸው ባለ ድርሻ አካላት ተወያይተውበት ውሳኔ እንደሚሰጥበት ገለፀው ቃለ ቡራኬ አስተላልፈዋል።ባንኩ የአስራት በኩራት ቁጠባ ሂሳብ ፕሮግራምን ያስተዋወቀው ህዝበ ክርስቲያኑ ሀይማኖታዊ ግዴታውን በቀላሉ ለመወጣት እንዲችል ለማገዝ መሆኑን የባንኩ የበላይ ሀላፊዎች አብራርተዋል፡፡በመርሐ ግብሩ ላይ ከልዩ ጽ/ቤቱ እና የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል። ምንጭ፡የምዕራብ አርሲ ሀገረ ስብከትየዐሥራት በኲራት ሒሳብ መለያዎች እና አገልግሎቱ የሚያስገኛቸውን ዝርዝር ልዩ ጥቅሞች፤ ከታች የሚገኘውን የቴሌግራም ቻነል ሊንክ በመጠቀም ይመልከቱ!

https://t.me/BoAEth/215

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Call Now Button