አቢሲንያ ባንክ የ ብር 2 ሚሊየን ድጋፍ ለፓርትነርሽፕ ፎር ፓስቶራሊስት ዴቨሎፕመንት አሶሴሽን ሰጠ፡፡

አቢሲንያ ባንክ የ ብር 2 ሚሊየን ድጋፍ ለፓርትነርሽፕ ፎር ፓስቶራሊስት ዴቨሎፕመንት አሶሴሽን ሰጠ፡፡

ባንካችን አቢሲንያ ፓርትነርሽፕ ፎር ፓሰቶራሊስት ዴቨሎፕመንት አሶሴሽን የተሰኘ መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት በሶማሌ ክልላዊ መንግሥት ሊበን ዞን የሚገኙ በድርቅ የተጎዱ 2 ወረዳዎችን መልሶ ለማቋቋም እየሠራ የሚገኘውን በጎ ተግባር ማገዝ ይቻል ዘንድ የብር 2 ሚሊዮን ድጋፍ አድርጓል፡፡
ድጋፉን በማስመልከት የተሰናዳው ዝግጅትም ሰኔ 15 ቀን 2014 ዓ.ም በባንካችን ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት የባንኩ የሸሪአ ቦርድ አማካሪ የሆኑት ሀጂ ኑረዲን ደሊል፣ የባንካችን ከወለድ ነፃ ብድር ትንተና ዳይሬክተር የሆኑት አቶ አብረሃም ረዲ እና የማኅበሩ የሥራ አመራሮች በተገኙበት ተከናውኗል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Call Now Button