18456

ምንም እንኳን ሀገራችን ኢትዮጵያ ዝቅተኛ ገቢ ካላቸው ሀገራት ብትመደብም ህዝቦቿ የራሳቸውን ኑሮ ለማሻሻል በሚያገኟቸው አነስተኛ ገቢ የተለያዩ አማራጮችን ሲጠቀሙ ይታያል፡፡ ከዚህም ውስጥ አንዱ ዕቁብ ሲሆን፣ በማኅበረሰባችንም ውስጥ ትልቁን ድርሻ ይወስዳል፡፡
የአቢሲንያ የዕቁብ የቁጠባ ሂሳብ በሚይዙዋቸው የአባላት ብዛት እና በሚሰበስቧቸው የገንዘብ መጠን ከፍተኛ፣ መካከለኛ እንዲሁም አነስተኛ በመባል የተመደቡ ሲሆን እንደ መጠናቸው የየራሳቸው መለያዎች እና የሚያስገኛቸው ጥቅሞች እንደሚከተሉት ቀርበዋል፡፡
እንዲሁም ዛሬ ዛሬ በሀገራችን የሚገኙ ዕድሮች ወትሮ ከተቋቋሙበት ዓላማ በዘለለ ለአባሎቻቸውና እንዲሁም ለማኅበረሰቡ የተለያዩ አገልግሎቶችን እየሰጡ ይገኛሉ፡፡ ይህንኑ ያላቸውን ማኅበራዊ ፋይዳ ከግምት ውስጥ በማስገባት ባንካችን አቢሲንያ በሀገራችን ተደራጅተው ለሚንቀሳቀሱ ዕድሮች የተሻለ አማራጮችን ይዞ ቀርቧል፡፡

 1. #የዕቁብቁጠባ ሂሳብBoA_Iqqub_Account 1.1 #ከፍተኛ የዕቁብሂሳብ መለያዎች
  🔰 ይህ የዕቁብ ሂሳብ የሚይዟቸው አባላት መጠን ብዙ እና የሚሰበሰበው የገንዘብ መጠን አንድ ሚሊዮን እና ከዚያ በላይ መሆን ይኖርበታል፡፡
  🔰የዚህ የቁጠባ ሂሳብ አባላት ሁሉም በንግድ እንቅስቃሴ ውስጥ ያሉና፤ የዚህ ዕቁብ ሰብሳቢው በማኅበረሰቡ ዕውቅና ያለውና የባንክ እንቅስቃሴው ጋር በደንብ የተዋወቁ ቢሆን ይመረጣል፡፡
  🔰ሁሉም የዕቁብ አባላት በአቢሲንያ ባንክ የተቀማጭ ሂሳብ ያላቸዉ ይሆናሉ፡፡
  🔰የዕቁቡ ሰብሳቢ የአባላቱን ክፍያ የሚሰበስብበት የእቁብ ሂሳብ በአቢሲንያ ባንክ ይከፍታል፡፡
  🔰ከዕቁብ ለመጀመሪያዎቹ ለአስር ተከታታይ ክፍያዎች ምንም ወጪ ከሂሳቡ አያደርግም፡፡
  🔰የዕቁቡ ሂሳብ ልዩ የቁጠባ ሂሳብ አይነት ሲሆን ይኸዉም የቁጠባና የተንቀሳቃሽ ሂሳቦች ባህሪያት ስለሚኖሩት ወለድ የሚታሰብበትና በቼክ የሚንቀሳቀስ ይሆናል፡፡
  🔰የዕቁቡ አባላት በየጊዜዉ የሚደረጉ ክፍያዎችን ከሂሳባቸዉ ተቀንሶ ወደ እቁብ ሂሳብ በጥሬ ገንዘብ ባንኩ ባቀረባቸው የኤሌክትሮኒክስ የመክፈያ ዘዴዎች ማስተላለፍ ይችላሉ፡፡
  🔰የዕቁብ ዕጣ የደረሰዉ አባል ባንኩ ዉስጥ ባለዉ ሂሳብ ገቢ ይደረግለታል፤
  1.2 #የከፍተኛየዕቁብ ሂሳብየሚያስገኛቸው ጥቅሞች
  🔰እስከ 2% በሚደርስ ቅናሽ የኦቨር ድራፍት ብድር ተጠቃሚ ያደርጋል፡፡
  🔰የገንዘብ አሰባሰብ ላይና ሌሎች ከዕቁቡ ጋር በተያያዙ ያሉ ድጋፎችን ባንኩ ያመቻቻል፡፡
  🔰ባንኩ የአባላት ቋሚ የክፍያ ትዕዛዞችን ያለ አገልግሎት ክፍያ ይሠራል፡፡
  🔰ባንኩ የዕቁብ ደብተሮችና መታወቂያ የመሳሰሉትን ለዕቁቡ በሚሆን መልክ በማዘጋጀት በስጦታ መልክ ያቀርባል፡፡
  🔰በዚህ የቁጠባ ሂሳብ የሚንቀሳቀሰው የገንዘብ መጠን ከአንድ ሚሊዮን ብር በላይ ሲሆን
  የ7.5% ወለድ እንዲሁም ከአንድ ሚሊዮን ብር በታች ሲሆን የ7.3% ወለድ
  ይታሰብበታል፡፡
  🔰ባንኩ እንደ አስፈላጊነቱ አባላቱ ዕቁብ የሚሰበስቡበት ቦታ ድረስ በመሄድ ገንዘቡን
  ተቀብሎ ወደ እቁብ ሂሳብ ገቢ ያደርጋል፡፡
  1.3 #የመካከለኛዕቁብ መለያዎች
  🔰በዚህ የቁጠባ ሂሳብ ተጠቃሚ መሆን የሚችሉት ቋሚ የሆነ ወርሃዊ ገቢ ያላቸው የመንግስት ወይንም መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት ሠራተኞች እንዲሁም ሌሎች ማናቸውም ቋሚ የሆነ ወርሃዊ ገቢ ያላቸው ይሆናሉ፡፡
  🔰የዕቁብ ሂሳቡ የተሻለ የወለድ ምጣኔ የሚታሰብበት የቁጠባ ሂሳብ ነዉ፡፡
  🔰የዕቁብ አባላት ክፍያ ከደሞዝ የሚሰበሰብ ከሆነ የመስሪያ ቤቱ የደሞዝ ክፍያ በባንኩ በኩል ይሆናል፡፡
  🔰ዕቁቡ ለመጀመሪያዎቹ ሦስት ተከታታይ ክፍያዎች የእጣ ክፍያ ወጪ አያደርግም፡፡
  1.4 #የመካከለኛዕቁብየሚያስገኛቸውልዩጥቅሞች
  🔰ከመደበኛው የቁጠባ ሂሳብ የተሻለ ወለድ ያስገኛል፡፡ በዚህም መሰረት የዚህ ዕቁብ ተቀማጭ ገንዘብ ከአንድ መቶ ሺህ ብር በታች ሲሆን የ 7.3% ወለድ እንዲሁም ከአንድ መቶ ሺ ብር በላይ ሲሆን 7.5% ወለድ ታሳቢ ይደረግበታል፡፡
  🔰ባንኩ ከዕድር አባላቱ ቋሚ ትዕዛዝ በመቀበል በየጊዜው ከአባላቱ ሂሳብ ተቀናሽ በማድረግ ወደ ዕቁቡ ሂሳብ ገቢ ያደርጋል፡፡
  1.5 #የአነስተኛዕቁብመለያዎች
  🔰በዚህ የቁጠባ ሂሳብ ተጠቃሚ መሆን የሚችሉት ቋሚ የሆነ ወርሃዊ ገቢ የሌላቸው ሆነው በየትኛውም አይነት የሥራ ዘርፍ የተሰማሩ የማኅበረሰብ ክፍሎች ሊሆኑ ይችላሉ፡፡
  1.6 #የአነስተኛዕቁብየሚያስገኛቸውጥቅሞች 🔰ከመደበኛው የቁጠባ ሂሳብ የተሻለ ወለድ ይኖረዋል፡፡ 🔰የዕቁብ አባላት የሙዳይ አቢሲንያ በግማሽ ክፍያ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ያስችላል፡፡ 1.7 #የዕቁብሒሳቡንለመክፈትመሟላትየሚገባቸውሰነዶች
  🔰በሁሉም የእቁብ አባላት የተፈረመ የመመስረቻ ጽሑፍ እና የመተዳደሪያ ደንብ፤
  🔰ልዩ የቁጠባ ሂሳቡን ለመክፈት የሚያስችል ቃለ-ጉባኤ፤
  🔰ለዕቁብ ሰብሳቢ ይህንን ዕቁብ እንዲከፍት እና እንዲያንቀሳቅስ ከዕድሩ የተሰጠ የድጋፍ ደብዳቤ፤
  🔰የባንክ ሂሳብ ማንቀሳቀስ የተፈቀደላቸዉ አባላት ጊዜው ያላለፈበት መታወቂያ፣ የታክስ መለያ ቁጥር (ለከፍተኛ ዕቁቦች ልዩ የቁጠባ ሂሳብ መክፈት ለፈለጉ) እና የቅርብ ጊዜ ፎቶግራፍ፤
 2. #የዕድርቁጠባ ሂሳብ BoA_Iddir_Account 2.1 #የዕድር የቁጠባ ሂሳብ መለያዎች
  🔰ከመደበኛው የቁጠባ ሂሳብ የተሻለ የወለድ መጠን ያስገኛል፡፡
  🔰የቁጠባ ሂሳቡ በዕድሩ ስም ወይንም በዕድሩ የበላይ አመራሮች ስም ሊከፈት ይችላል፡፡
  🔰እያንዳንዱ የዕድር አባላት የራሳቸውን ሂሳብ በመክፈት ለዚሁ ሂሳብ የተዘጋጁትን ጥቅማጥቅሞች እንዲያገኙ ያስችላቸዋል፡፡
  🔰ባንኩ በሚሰጠው ቋሚ ትዕዛዝ፣ በጥሬ ገንዘብ ወይንም በባንኩ ባሉ በኤሌክትሮኒክ የመክፈያ ዘዴዎች የዕድሩ ገንዘብ የሚሰበሰብ ይሆናል፡፡
  🔰እንደአስፈላጊነቱ ባንኩ በፋይናንስ ዙሪያ የምክር አገልግሎት የሚሰጥ ይሆናል፡፡
  2.2 #የዕድርየቁጠባሂሳብየሚያስገኛቸውጥቅሞች
  🔰የቁጠባ መጠኑ ከብር 1 ሚሊዮን በታች ለሆነ ሂሳብ 7.5% የሆነ የወለድ ምጣኔ ሲታሰብ ሂሳቡ ከብር 1 ሚሊዮን በላይ ሲሆን ደግሞ 8.0% የወለድ ምጣኔ ይታሰባል፡፡
  🔰በ1% የወለድ ቅናሽ የብድር አገልግሎት ይመቻቻል፡፡
  🔰አማካኝ የተቀማጭ ሂሳቡን መነሻ በማድረግ በ0.5% የሚሰላ ዓመታዊ ቦነስ ያስገኝለታል፡፡
  🔰በየዓመቱ የባንኩ ዓርማ የያዙ የማስታወቂያ ቁሳቁሶች እንደ ዣንጥላ፤ አጀንዳ፤ የእድር አባላቱ መታወቂያና የመሳሰሉትን ለዕድሩ በስጦታ መልክ ይበረከትለታል፡፡
  2.3 #የዕድርሒሳቡን ለመክፈትመሟላትየሚገባቸው ሰነዶች
  🔰ይህንን የቁጠባ ሂሳብ ለመክፈት የሚያስችል የድጋፍ ደብዳቤ፤
  🔰የዕድር አባላቱን ፊርማ የያዘ የመመስረቻ ፅሁፍ እና ቃለ-ጉባኤ፤
  🔰በቃለ ጉባኤ የተያዘ የዕድር ኃላፊዎች ሂሳብ መክፈት የሚያስችል ደብዳቤ እንዲሁም
  🔰የቁጠባ ሂሳቡን እንዲያንቀሳቅስ በዕድሩ የሚወከሉ የዕድሩ የበላይ አመራሮች የታደሰ መታወቂያና የቅርብ ጊዜ ፎቶግራፍ

ለበለጠ_መረጃ:

ነፃ የስልክ መስመር: 8397
ስልክ፤ +251-116 68 61 40

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Call Now Button