አቢሲንያ ባንክ /አ.ማ/ ለሰጠው ብድር በዋስትና የያዘውንና በሠንጠረዡ የተመለከቱትን ንብረቶች በአዋጅ ቁጥር 97/90 (እንደተሻሻለው) መሠረት ንብረቶቹ ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ተጫራቾች ለጨረታ ከመቅረባቸው በፊት የሚከተሉትን ደንቦች መገንዘብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ንብረት የጨረታ መነሻ ዋጋውን ¼ (አንድ አራተኛ) በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይም ሲ.ፒ.ኦ በአቢሲንያ ባንክ (አ.ማ) ስም በማሰራት ለጨረታ ማስከበሪያ በማስያዝ በጨረታው ለመሳተፍ ይችላሉ፡፡
- የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱ ከባንኩ በደብዳቤ ከተገለጸለት ቀን ጀምሮ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ በ15 (አስራ አምስት) ቀናት ውስጥ አጠቃሎ ከፍሎ በጨረታ ያሸነፈበትን ንብረት/ንብረቶች መረከብ ይኖርበታል፡፡ በእነዚህ ቀናት ውስጥ ካልከፈለ ጨረታው ተሰርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል፡፡ በጨረታው ለተሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ ይመለስላቸዋል፡፡
- ተበዳሪው/መያዣ ሰጪው በሐራጁ ቀንና ሰዓት በቦታው መገኘት ይችላሉ፡፡ ነገር ግን ባይገኙ ሐራጁ በሌሉበት ይካሄዳል፡፡
- የጨረታው አሸናፊ ከሚገዛው ንብረት ጋር የተያያዙ ማናቸውም ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎችን ፣ ግብር ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ 15% እንዲሁም ከስም ዝውውር ጋር የሚገናኙ ማናቸውም ወጪዎችንም ገዢ ይከፍላል፡፡ ውዝፍ የሊዝ ክፍያ ካለ ባንኩ የሚከፍል ሲሆን ቀሪ የሊዝ ክፍያ ገዢ ከሚመለከተው የመንግስት አካል ጋር ይዋዋላል፡፡
- ንብረቶቹን በሥራ ሰዓት ፕሮግራም አሲዞ ለመጎብኘት ወይም ለማየት ይቻላል፡፡
- በባንኩ ብድር ፖሊሲ እና መመሪያ መሠረት መስፈርቱን ለሚያሟሉ የጨረታው ከፍተኛ ዋጋ አቅራቢዎች ባንኩ ከፊል ብድር ሊሰጥ ይችላል፡፡
- የጨረታው ቦታ አዲስ አበባ ከተማ ቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ 4 ህብረት ባንክ አ.ማ ዋና መስሪያ ቤት ጎን ካለው አልፓውሎ ህንጻ 3ኛ ፎቅ በባንኩ ህግ መምሪያ ነው፡፡
- ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0115-150711 እና 0115 54 67 37/36 አ.አ በመደወል መጠየቅ ይቻላል፡፡
- ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
t.q$ | ከተበዳሪው የሚፈለግበት ቀሪ ዕዳ | የመያዣ ስጪው ስም | የንብረቱ ዓይነትና አገልግሎት | የቦታው ስፋት | የባለቤትነት ማረጋገጫ ካርታ ቁጥር | ንብረቱ የሚገኝበት አድራሻ | የጨረታ መነሻ ዋጋ በብር | ጨረታው የሚካሄድበት ቀን | የምዝገባ ሰዓት | የጨረታ ሰዓት | ጨረታው የወጣበት ጊዜ |
1 | እስከ ጥር 20 ቀን 2012 ብር 4,328,154.23 | ተበዳሪው | በግንባታ ላይ ያለ G+2+T መኖሪያ ቤት | 230 ካ.ሜ | ቦሌ/ሊዝ/ጨ4/43/ 11/14/10654/00 | በአዲስ አበባ ከተማ ቦሌ ክ/ከ ወረዳ 10 | 7,019,400.00 | ሐምሌ 6 ቀን 2013ዓ.ም | 4:30-5:30 | 5፡30-6፡00 | በድጋሚ |
2 | እስከ ጥር 04 ቀን 2013 ዓ.ም ብር 7,638,182.27 | ተበዳሪው | G+2 እና G+1 መኖሪያ ቤት | 300 ካ.ሜ | AA000090602133 | አ.አ ኮ/ቀራንዮ ክ/ከተማ፣ወረዳ 06 | 8,180,860.78 | ሐምሌ 8 ቀን 2013ዓ.ም | 4:30-5:30 | 5:30-6:00 | ለመጀመሪያ ጊዜ |
3 | እስከ ታህሳስ 03 ቀን 2012 ዓ.ም ብር 4,335,283.01 | ተበዳሪው | መጋዘን | 500 ካ.ሜ | 370/3101/97 | በኦ/ብ/ክ/መንግስት ሰንዳፋ፣ከተማ ቀበሌ 01 | 1,855,000.00 | ሰኔ 30 ቀን 2013 ዓ.ም | 4፡30-5፡30 | 5፡30-6፡00 | ለመጀመሪያ ጊዜ |
4 | እስከ እ.ኤ.አ እስከ 13/03/2019 ድረሰ ብር 2,125,393.47 | ተበዳሪው | G+2 መኖሪያ ቤት | 250 ካ.ሜ | ግ/20/4/1159/2003 | ባህር ዳር ቀበሌ 14 | 3,811,710.00 | ሐምሌ 15 ቀን 2013 ዓ.ም | 4፡30-5፡30 | 5፡30-6፡00 | ለሁለተኛ ጊዜ |
Leave a Reply