አቢሲንያ ባንክ /አ.ማ/ ለሰጠው ብድር በዋስትና የያዛቸውንና በሠንጠረዡ የተመለከቱትን ንብረቶች በአዋጅ ቁጥር 97/90 (እንደተሻሻለው) መሠረት ንብረቶቹ ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ተጫራቾች ለጨረታ ከመቅረባቸው በፊት የሚከተሉትን ደንቦች መገንዘብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ንብረት የጨረታ መነሻ ዋጋውን ¼ (አንድ አራተኛ) በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይም ሲ.ፒ.ኦ በአቢሲንያ ባንክ (አ.ማ) ስም በማሰራት ለጨረታ ማስከበሪያ በማስያዝ በጨረታው ለመሳተፍ ይችላሉ፡፡
- የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱ ከባንኩ በደብዳቤ ከተገለጸለት ቀን ጀምሮ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ በ15 (አስራ አምስት) ቀናት ውስጥ አጠቃሎ ከፍሎ በጨረታ ያሸነፈበትን ንብረት/ንብረቶች መረከብ ይኖርበታል፡፡ በእነዚህ ቀናት ውስጥ ካልከፈለ ጨረታው ተሰርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል፡፡ በጨረታው ለተሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ ይመለስላቸዋል፡፡
- ተበዳሪው/መያዣ ሰጪው በሐራጁ ቀንና ሰዓት በቦታው መገኘት ይችላሉ፡፡ ነገር ግን ባይገኙ ሐራጁ በሌሉበት ይካሄዳል፡፡
- የጨረታው አሸናፊ ከሚገዛው ንብረት ጋር የተያያዙ ማናቸውም ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎችን ፣ ግብር ፣ በተጠቀሱት ንብረቶች ላይ የተጨማሪ እሴት ታክስ 15% እንዲሁም ከስም ዝውውር ጋር የሚገናኙ ማናቸውም ወጪዎችንም ገዢ ይከፍላል፡፡ ውዝፍ የሊዝ ክፍያ ካለ ባንኩ የሚከፍል ሲሆን ቀሪ የሊዝ ክፍያ ገዢ ከሚመለከተው የመንግስት አካል ጋር ይዋዋላል፡፡
- ንብረቶቹን በሥራ ሰዓት ፕሮግራም አሲዞ ለመጎብኘት ወይም ለማየት ይቻላል፡፡
- በባንኩ ብድር ፖሊሲ እና መመሪያ መሠረት መስፈርቱን ለሚያሟሉ የጨረታው ከፍተኛ ዋጋ አቅራቢዎች ባንኩ ከፊል ብድር ሊሰጥ ይችላል፡፡
- የጨረታው ቦታ አዲስ አበባ ከተማ ቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ 4 ህብረት ባንክ አ.ማ ዋና መስሪያ ቤት የነበረው ጎን ካለው አልፓውሎ ህንጻ 3ኛ ፎቅ በባንኩ ህግ መምሪያ ነው፡፡
- ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0115-150711 እና 0115 54 67 37 አ.አ በመደወል መጠየቅ ይቻላል፡፡
- ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ytbĶW SM | ከተበዳሪው የሚፈለግበት ቀሪ ዕዳ | የመያዣ ስጪው ስም | የንብረቱ ዓይነትና አገልግሎት | የቦታው ስፋት | የባለቤትነት ማረጋገጫ ካርታ ቁጥር | ንብረቱ የሚገኝበት አድራሻ | የጨረታ መነሻ ዋጋ በብር | ጨረታው የሚካሄድበት ቀን | የምዝገባ ሰዓት | የጨረታ ሰዓት | ጨረታው የወጣበት ጊዜ | |
1 | አቶ ሞላ ተመስገን | እስከ ሚያዝያ 13 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ ብር15,400,000.00 | ተበዳሪው | G+2 መኖሪያ ቤት | 127.3 ካሜ | AA0000907013827 | አዲስ አበባ ኮልፌ ቀራንዮ ወረዳ 7 | 6,410,193.40 | ሐምሌ 20 ቀን 2013 ዓ.ም | 4፡30-5፡30 | 5፡30-6፡00 | ለመጀመሪያ ጊዜ |
2 | አቶ ዮናስ ተሰማ | እስከ ጥር 24 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ ብር1,369,232.41 | ተበዳሪው | ኮንዶሚኒየም የንግድ | 55.78ካሜ | 01633/1 | አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ሳሎጎራ | 1,408,418.62 | ሐምሌ 29 ቀን 2013 ዓ.ም | 4፡30-5፡30 | 5፡30-6፡00 | ለመጀመሪያ ጊዜ |
3 | አቶ ዘነበ ተክሉ | እስከ ግንቦት 13 ቀን 2013ዓ.ም ድረስ ብር 1,507,311,66 | ተበዳሪው | መኖሪያ ቤት | 200 ካ.ሜ | 756/243/2002 | በኦሮ/ብ/ክ/መ ሰንዳፋ ከተማ ቀበሌ 01 | 782,431.17 | ሐምሌ 22 ቀን 2013 ዓ.ም | 4፡30-5፡30 | 5፡30-6፡00 | ለመጀመሪያ ጊዜ |
4 | አቶ አብርሃም ስሜ | እስከ ግንቦት 29 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ ብር 1,302,004.47 | ወ/ሮ ዮርዳኖስ ፍቃዱ | መኖሪያ ቤት | 105 ካ.ሜ | 1056/2000 | አሮ/ክ/መንግስት አዳማ ከተማ፣ ቀበሌ 14 | 977,340.00 | ሐምሌ 29 ቀን 2013 ዓ.ም | 4፡30-5፡30 | 5፡30-6፡00 | በድጋሚ |
5 | ዶ/ር መድሃኔ ሃጎስ | እስከ ግንቦት 27 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ ብር 38,440,035.96 | ተበዳሪው | B+M+5 Mixed (ቅይጥ) | 153 ካ.ሜ | AA000060304874 | አዲስ አበባ ቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 03 ብሎክ BL-03-64451 | 23,972,123.16 | ሐምሌ 26 ቀን 2013 ዓ.ም | 4፡30-5፡30 | 5፡30-6፡00 | ለመጀመሪያ ጊዜ |
Leave a Reply