አቢሲንያ ባንክ ከቪዛ ጋር በመተባበር በኳታር እየተከናወነ የሚገኘው የ2022 የፊፋ የዓለም ዋንጫን አስመልክቶ የሽልማት መርሐ-ግብር እንዲሁም የዕጣ አወጣጥ ሥነ ሥርዓቱን በብሔራዊ ሎተሪ አዳራሽ ማካሄዱ ይታወቃል፡፡ ሆኖም ለባለዕድለኞቹ ትላንት ኅዳር 19 ቀን 2015 ዓ.ም በሚሊኒየም አዳራሽ ባዘጋጃው ደማቅ መርሀ ግብር ወደ ኳታር የሽኝት ዝግጅት አከናውኗል፡፡
ይህ ሽልማት ባለዕድል ደንበኛው ከሚመርጡት አንድ የቤተሰብ አባል ወይም ጓደኛ ጋር የመጀመሪያው ዙር የማጣሪያ ጨዋታን ለመመልከት ወደ ኳታር እንዲጓዙ የሚያስችላቸው ሲሆን፣ በተጨማሪም ባለ 5 ኮኮብ ሆቴል ውስጥ ለሁለት ምሽቶች ማረፊያ፣ የገበያ አበል፣ ከመድረክ ጀርባ በቅርበት ትእይንት የማየት ልምድ እና ሁለት ተከታታይ ጨዋታዎችን የማየት እድል ያካተተ ነው፡፡
Leave a Reply