የ “እችላለሁ” ዘመቻ የውድድር ድምፅ አሰጣጥ

የ “እችላለሁ” ዘመቻ የውድድር ድምፅ አሰጣጥ

በየአመቱ ማርች 8 የሚከበረውን የሴቶች ቀን አስመልክቶ ሴት ባለተሰጥኦዎችን በማሳተፍ በባንካችን ሲካሄድ የነበረው የ “እችላለሁ” ዘመቻ የውድድር ሥራዎች ማቅረቢያ ቀን እሑድ መጋቢት 11 ቀን 2014 ዓ.ም. የተጠናቀቀ ሲሆን፣ በውድድሩም 318 በግጥም፣ እንዲሁም 33 በድምፅ በአጠቃላይ 351 ተሳታፊዎች ስራቸውን አቅርበዋል፡፡ ለውድድር ከቀረቡት የሙዚቃና የግጥም ስራዎች ውስጥም ከእያንዳንዱ ዘርፍ አስር አስር ስራዎች በባለሙያዎች ተገምግመው ለመጨረሻው የታዳሚዎች ምርጫ የተለዩ ሲሆን፣ አርቲስት ጌትነት እንየው፣ ገጣሚ ረድኤት ተረፈ እና ገጣሚ የሺወርቅ ወልዴ የግጥም ስራዎችን በመገምገም፣ እንዲሁም ሙዚቀኛ የሹምነሽ ታዬ እና ሙዚቀኛ ሜሮን ረጋሳ የሙዚቃ ስራዎችን በመገምገም ስራ ላይ ተሳትፈዋል፡፡በቀጣይም ከእያንዳንዱ ማለትም ከግጥምና ሙዚቃ ዘርፍ ከአንደኛ እስከ ሶስተኛ የሚወጡት ባለተስጥኦዎች በአድማጭና አንባቢ ድምፅ 50% ፣እንዲሁም በዳኞች 50% ነጥብ የሚለዩ ይሆናል፡፡
በመሆኑም በመጀመሪያ ዙር የተለዩት አስር የግጥም ስራዎች በፌስ ቡክ ገፃችን ላይ የቀረቡ በመሆኑ ይህን ሊንክ በመጠቀም https://bit.ly/3IS5Pc8 ከዛሬ መጋቢት 21፣ 2014 እስከ መጋቢት 23 ቀን 2014 ባለው ጊዜ ውስጥ የተወዳዳሪዎችን በምስሉ ላይ የሚገኘውን መለያ ኮድ በመጠቀምና የመረጣችሁትን በፌስ ቡክ ኮመንት ሥፍራ ላይ በመፃፍ የድምፅ አሰጣጥ ተሳትፎ እንድታደርጉ እንጋብዛለን፡፡
በቀጣይም የተለዩት የሙዚቃ ስራዎች እንዲሁ ለምርጫ የሚቀርቡ በመሆኑ ይከታተሉ፡፡
መልካም ዕድል ለተሳታፊዎች!

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Call Now Button