ባንካችንና ቪዛ የዓለም ዋንጫን ለመታደም ዕጣ የወጣላቸዉን የ4ኛ ዙር ዕድለኞች ይፋ አደረጉ

ባንካችንና ቪዛ የዓለም ዋንጫን ለመታደም ዕጣ የወጣላቸዉን የ4ኛ ዙር ዕድለኞች ይፋ አደረጉ

ባንካችን አቢሲንያ እና ቪዛ ደንበኞችን ለማበረታታት ብሎም ለመሸለም የ2026 ፊፋ ዓለም ዋንጫን በስፍራው በአካል ተገኝተው ለመከታተል የሚያስችል ዕጣ የወጣላቸዉን የአራተኛ ዙር 4 ዕድለኞች በጋራ ይፋ አደረጉ።

ትናንት መጋቢት 29  ቀን 2018 ዓ.ም በዋናው መ/ቤት የባንካችን የሥራ ሐላፊዎችና የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት ታዛቢዎች በተገኙበት መርሐ ግብር ላይ የባንካችን የኢኖቬሽን እና ቢዝነስ ዴቨሎፕመንት ዳይሬክተር አቶ ዳኛቸው አስናቀ የዕጣ ማውጣቱን ሥነ-ሥርዓት በይፋ አስጀምረዋል።

በወጣው ዕጣ መሠረትም 3 የባንካችን የምስራቅ አዲስ ዲስትሪክት ደንበኞች (የዕጣ ቁጥር 700023072፣ 700024980 እና 300021556)  እንዲሁም 1 የባህርዳር ዲስትሪክት ደንበኛ (የዕጣ ቁጥር 700029886) በድምሩ 4 የባንካችን ደንበኞች ዕድለኞች ሆነዋል።

በዚህ የሽያጭ ዘመቻ ጠንካራ የደንበኞች ተሳትፎ የታየ ሲሆን፣ ባለፈው አንድ ሳምንት ብቻ ከ10,800 በላይ ኩፖኖች የአቢሲንያ ባንክ ቪዛ ካርዶችን በመጠቀም ከ1,000 ብር በላይ ግብይቶችን ለፈጸሙ ደንበኞች ተልከዋል።

ይህ የሽያጭ ዘመቻ በባንካችን እና በቪዛ መካከል በመላው ኢትዮጵያ የክፍያ ስርዓቶችን ፍጥነት፣ ደህንነት እና ቅልጥፍና ለማሻሻል ያለመ ሰፊ ስትራቴጂካዊ ትብብር አካል ነው።

እስካሁን በነበሩ 4 ዙሮች 16 ደንበኞች የዚህ የሽያጭ ዘመቻ ዕድለኞች የሆኑ ሲሆን፣ ቀሪዎቹ 4 ዕጣዎችም በቀጣይ ሳምንታት የሚወጡ ይሆናል።

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Call Now Button