ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

አቢሲንያ ባንክ /አ.ማ/ ለሰጠው ብድር በዋስትና የያዛውንና በሠንጠረዡ የተመለከተውን ንብረት በአዋጅ ቁጥር 97/90 (እንደተሻሻለው) መሠረት ንብረቱ ባለበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ተጫራቾች ለጨረታ ከመቅረባቸው በፊት የሚከተሉትን ደንቦች መገንዘብ ይኖርባቸዋል፡፡

  • ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ንብረት የጨረታ መነሻ ዋጋውን ¼ (አንድ አራተኛ) በአቢሲንያ ባንክ (አ.ማ) ስም ሲ.ፒ.ኦ በማሰራት ለጨረታ ማስከበሪያ በማስያዝ በጨረታው ለመሳተፍ ይችላሉ፡፡
  • የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱ ከባንኩ በደብዳቤ ከተገለጸለት ቀን ጀምሮ በ15 (አስራ አምስት) ቀናት ውስጥ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ አጠቃሎ ከፍሎ በጨረታ ያሸነፈበትን ንብረት/ንብረቶች መረከብ ይኖርበታል፡፡ በእነዚህ ቀናት ውስጥ ካልከፈለ ጨረታው ተሰርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል፡፡ በጨረታው ለተሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ ይመለስላቸዋል፡፡
  • ተበዳሪው/መያዣ ሰጪው በሐራጁ ቀንና ሰዓት በቦታው መገኘት ይችላሉ፡፡ ነገር ግን ባይገኙ ሐራጁ በሌሉበት ይካሄዳል፡፡
  • የጨረታው አሸናፊ ከሚገዛው ንብረት ጋር የተያያዙ ማናቸውም ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎችን ፣ ግብር ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ በሚያስከፍሉ ንብረቶች ሽያጭ ላይ የተጨማሪ እሴት ታክስ 15% እንዲሁም ከስም ዝውውር ጋር የሚገናኙ ማናቸውም ወጪዎችንም ገዢ ይከፍላል፡፡ ውዝፍ የሊዝ ክፍያ ካለ ባንኩ የሚከፍል ሲሆን ቀሪውን የወደፊት የሊዝ ክፍያ ገዢ ይከፍላል፡፡
  • ንብረቶቹን በሥራ ሰዓት ፕሮግራም አሲዞ ለመጎብኘት ወይም ለማየት ይቻላል፡፡
  • በባንኩ ብድር ፖሊሲ እና መመሪያ መሠረት የብድር መስፈርቱን ለሚያሟሉ የጨረታው ከፍተኛ ዋጋ አቅራቢ/አቅራቢዎች ባንኩ ከፊል ብድር ሊሰጥ ይችላል፡፡
  • የጨረታው ቦታ በአዲስ አበባ ከተማ ቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ 4 ላንቻ አካባቢ ህብረት ባንክ አ.ማ ዋና መስሪያ ቤት ከነበረው ህንጻ ጎን ካለው አልፓውሎ ህንጻ 3ኛ ፎቅ በባንኩ ህግ መምሪያ ነው፡፡
  • ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0115-150711 እና 0115 54 67 37 አ.አ በመደወል መጠየቅ ይቻላል፡፡
  • ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Call Now Button