ተለዋዋጭ በሆነው የኑሮ ሁኔታ ውስጥ ሴቶች ጠንክረው እንዲወጡ!

ተለዋዋጭ በሆነው የኑሮ ሁኔታ ውስጥ ሴቶች ጠንክረው እንዲወጡ!

በየዘመናቱ እየተነሡ በታሪክ መዝገብ ላይ ደምቀው የተጻፉ እንስት ጀግኖች ብዙ አሉን፡፡ አገርን በመገንባት ሒደት ከመሳተፍ እስከ ድንቅ አሻራ እና ቅርሶችን ያሳረፉ፤ በዓለም መድረክ ላይ ኢትዮጵያን ከፍ አድርገው ስሟን ያስከበሩ እልፍ ሴቶች አሉን፡፡

ከክርስቶስ ልደት በፊት 1000 ዓ.ዓ ወደ ኋላ ተጉዘን የምናገኛት ንግሥተ ሳባ፤ ከዛሬ 400 ዓመታት የነበረችው ንግሥት ወለተ ጴጥሮስ፤ ብዙም ሳንርቅ 100 ዓመታትን ተጠግተን የምናገኛት እቴጌ ጣይቱ በትረ መንግሥታቸውን ከመጨበጥ አልፈው አገርን በሰላም መምራታቸውን ስናስብ ሴቶች ሀገር የማስተዳደር ብቻም ሳይሆን ለመጪው ጊዜ መንገድ ጠራጊዎች እንደሆኑ ጭምር እንረዳለን፡፡

ሴቶችን ማጎልበት፤ በራስ የመተማመን እንዲጨም ማበረታት፤ የራሳቸውን ምርጫ የመወሰን ችሎታ እና በሌሎች ማኅበራዊ ለውጦች ላይ ተጽእኖ የማድረግ ብቃታቸውን እንዲያድግ ከጉያችን ያሉ ዕንቁዎቻችን ምርጥ ምሳሌዎቻችን ናቸው፡፡ እነዚህ እንቁዎቻችን በሥራ ፈጠራ አንቱታን ከማበርከት አልፈው ለሌሎች ወገኖቻችን የሥራ ዕድል በመፍጠር በሀገር ውስጥም በውጪ እያበሩ ይገኛሉ፡፡ እናንተስ አሁን እንዴት የበለጠ ለማደግ እና ለመፍካት አስባችኋል??..

ተጽዕኖ ፈጣሪዎችን መፍጠር ሀገራዊ ሓላፊነት ከመሆንም በላይ ተፈጥሮአዊ ነው፡፡ ይህንን የተገነዘበው ባንካችን አቢሲንያ ከመርሕ ባለፈ የሴቶችን ተፈጥሮ ከአይቻልም ባይነት በማላቀቅ አቅማቸውን በጉልህ እንዲያወጡ አጥብቆ እየተጋ ነው፡፡ ለዚህም ማረጋገጫ ወደ ስኬት ጎዳና የሚያራምዳቸውን እና ከማንም ልቀው እነዲታዩ የሚያደርጋቸውን ዕድል “አደይ ልዩ የሴቶች የቁጠባ አገልግሎት” እንካችሁ ካለን ሰነበተ፡፡ አደይ ለሴቶች ብቻ በልዩ ሁኔታ የተዘጋጀ የቁጠባ ሒሳብ፤ ከአቢሲንያ ለሴቶች የተሰጠ ስጦታ ምርጥ ስጦታ፡፡

ሴቶች በኢትዮጵያ ማኅበረሰብ ውስጥ የሚጫወቱት ሚና ከፍተኛ በመሆኑ እጃቸው ላይ ያለውን ትንሽ ገንዘብ በማመጣጠን ቤትን ማስተዳደር ያውቁበታል፡፡ ይህን ተፈጥሮአዊ ጥበብ የተገነዘበው ባንካችን የሴቶች ሚና ከፍ የሚያደርግ ምርጥ መላ አመቻችቷል፡፡ ጥረትዎን በድካም እንዳይቀር የግል ንግድዎን የሚሳድጉበት ከከፍተኛ ወለድ ጋር ያቀረብልዎ ልዩ የቁጠባ ሒሳብ አደይ፤ እነሆ ገጸ በረከቶቹ

  • የመቆጠብ አቅምን በመፍጠር ለስኬት ያበቃዎታል፤
  • የኤቲኤም ዴቢት ካርድ በነጻ ይሰጣል፤
  • ባንካችን ስምምነት ባደረገባቸው የአገልግሎቶች ሰጪ ድርጅቶች ጋር ግዢ ሲፈጽመኑ በተለየ ሁኔታ የዋጋ ቅናሽ ያደርጋል፤
  • በየቀኑ እስከ 15,000 ብር ከኤቲኤም ገንዘብ ማውጣት ይችላሉ፤
  • እስከ 25,000 ብር ድረስ ለሚቆጥ ሴቶች የስጦታ ሰርተፍኬት ይቀበላሉ፤
  • ከ500 ሺህ ብር በላይ ተቀማጮች ገንዘብ ላላቸው ቅድሚያ ከባንኩ አገልግሎት ማግኘት የሚያስችል ልዩ መታወቂያ ካርድ ያገኛሉ፡፡

“ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በላይ የሆኑ ሴቶች የቁጠባ ሒሳብ በመክፈት የልዩ አገልግሎቱና ጥቅሞቹ ተጋሪ ይሁኑ። ህልምዎና ፍላጎትዎ እንዲሳካ የአደይ ቁጠባን ይጠቀሙ፡፡”

በሚለዋወጥ የተፈጥሮ ሕግ ውስጥ እንስቶች ጠንክረው እንዲዘልቁ ያለመታከት እንሠራለን፡፡ አቢሲንያ ትጉኃን የሚያተጋ፡፡

ምኒልክ ብርሃኑ

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Call Now Button