ባንካችን አቢሲንያ ከደቡብ አፍሪካው አብሳ ባንክ (Absa Corporate and Investment Bank) ጋር ሚያዚያ 26 ቀን 2018 ዓ.ም በዋናው መ/ቤት የስብሰባ አዳራሽ የልምድ ልውውጥ አካሄደ።
በዚህ እርስ በርስ የመማማር እና የልምድ ልውውጥ መድረክ ላይ የአብሳ ባንክ የአመራር ብቃት ማሳደጊያ መርሐ ግብር (Absa Development Initiative – ADI) አካል የሆኑ 30 ከፍተኛ ሥራ አስኪያጆች እና ዳይሬክተሮች ተገኝተዋል።
በመድረኩ ላይ የባንካችን አመራሮች የዲጂታል ባንኪንግ እና ኒዮ-ባንኪንግ ጉዞ፣ ባንካችን ከአመሠራረት ጀምሮ አሁን እስከ ደረሰበት ደረጃ ስላለው አጠቃላይ ሁኔታ፣ የፋይናንስ ተደራሽነትን ማሳደግ በሚቻልባቸው መንገዶች ላይ፣ከወለድ ነፃ ባንክ ለፋይናንስ ዘርፉ ዕድገት እያበረከተ ስላለው አስተዋጽኦ እንዲሁም በሌሎች ቁልፍ ጉዳዮች ላይ ገለጻ አድርገዋል ።
ዝርዝር ገለጻዎቹን ተከትሎም ከአብሳ ባንክ የማኔጅመንት አባላት በርካታ ጥያቄዎች እና አስተያየቶች የተሰነዘሩ ሲሆን፣ የባንካችን አመራሮችም ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል።
አብሳ ባንክ በአፍሪካ አህጉር በዘርፉ ካለው ሰፊ ተሞክሮ አንጻር ይህ መድረክ ለሁለቱም ተቋማት ጠቃሚ የሆኑ የስትራቴጂክ ሀሳቦች የተለዋወጡበት ሆኖ ተጠናቅቋል።








Leave a Reply