ባንካችን የዓለም ዋንጫን አስመልክቶ ባዘጋጀው የሽልማት ፕሮግራም ዕድለኛውን ሸለመ

ባንካችን የዓለም ዋንጫን አስመልክቶ ባዘጋጀው የሽልማት ፕሮግራም ዕድለኛውን ሸለመ

ባንካችን በሁለተኛው ዙር 2026 ፊፋ ዓለም ዋንጫን አስመልክቶ ባዘጋጀው የሽልማት መርሀ ግብር የላፕቶፕ ዕድለኛ ለሆኑት ደንበኛ ትናንት ሰኔ 11 ቀን 2018 ዓ.ም.  ሽልማታቸውን አስረክቧል።

ባንካችን ከቪዛ ጋር በመተባበር በመጀመሪያው ዙር ደንበኞች የአቢሲንያ ቪዛ ካርድን ተጠቅመው ግብይት ሲፈጽሙ የ2026 ፊፋ ዓለም ዋንጫን በቀጥታ የመመልከት ዕድል የሚያስገኝላቸውን ታላቅ የሽልማት ፕሮግራም አዘጋጅቶ የነበረ ሲሆን፣ ዕድለኛ ደንበኞችም ጨዋታውን እየታደሙ ይገኛሉ፡፡

በሁለተኛው ምዕራፍም ደንበኞች የአቢሲንያ ቪዛ ካርዳቸውን ተጠቅመው ሲገበያዩ እና ሽልማት የሚያስገኝ ጨዋታ ሲጫወቱ የሚሸልም ሲሆን ቀደም ብሎም ሁለት ደንበኞችን ዘመናዊ ስልክ እና የ10,000 ብር ፕሪፔይድ ካርድ መሸለሙ ይታወሳል።

ትናንት በዋናው መ/ቤት የስብሰባ አዳራሽ በተደረገው የሽልማት ሥነ ስርዓት የመካከለኛው አዲስ ዲስትሪክት ሳር ቤት ቅርንጫፍ ደንበኛ ለሆኑት አቶ ተምኪን አሊ የባንካችን የካርድ ባንኪንግ ሥራ አስኪያጅ አቶ አንሙት ደሳለው ሽልማቱን አስረክበዋል።

Call Now Button